በጃፖን ካሳማ ከተማ ለጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ በሚካሄደው ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ለመካፈል በፌዴሬሽናችን ተ/ም/ ፕሬዘዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ የተመራ ልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው ያቀና ሲሆን የቶኪዮ ኦሎምፒክና ፖራኦሎምፒክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሀሺሚቶ ሴኮ እና በጃፖን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተ/ብርሃን ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በቶኪዮ ኦሎምፒክ እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ተካሂዷል። በዚህ ጉዞ ላይ የሻ/ል አበበ ቢቂላ ወንድ ልጅ የትናየት አበበ የልኡኩ አባል ሆኖ በማየታቸው ለጃፓናውያንና ለውድድሩ አዘጋጆች ከፍተኛ ኩራት፣ አድናቆተትና ግርምት ፈጥሯል። በመጨረሻም ክብርት ኮ/ር ደራርቱ አበበ ቢቂላን ለመዘከር በጃፖን መንግስት ውድድር በመዘጋጀቱና ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል በፌዴሬሽናችን ስም ምስጋና አቅርበዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተ/ም/ፕሬዝዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉና የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ ከጃፓን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጋር በአትሌቲክስ ልማት ዙሪያ በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

እሁድ 05/0412012  በጃፓን ካሳማ በተካሄደው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ውድድር በሁለቱም ፆታ ሃገራችንን የወከሉት አብዮት አብነትና እታለማሁ ስንታየሁ ሲያሸንፋ ውድድሮቹን ኮ/ር ደራርቱ፣ አቶ ቢልልኝና የሻ/ል አበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ አስጀምረዋል።

Similar Posts
Latest Posts from