የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአማራ ክልል ምዕ/ጎ/ዞን የሚገኙትን የቲሊሊ እና የፈረስ ቤት አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ካምፖችን ሰኔ 5 እና 10/2011 ዓ. ም ጎበኘ።

ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር የአማራ ክ/አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ አቶ አዱኛ ይግዛው የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር፣ አቶ ቢልልኝ መቆያ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊና የአካባቢው አመራሮች በተገኙበት የካምፑ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ አሰልጣኝ ያረጋል ሞላ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በተለይም የአካባቢው ተወላጅ ባለሃብቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የአትሌቲክስ ስፖርቱ አፍቃሪዎች እነዚህን የፈረስ ቤትና የቲሊሊ ካምፖች (በአየር ንብረታቸው ዳግማዊ በቆጂ ሊባሉ የሚችሉትን) እና በተለይ ፈረስ ቤት ከባህር ጠለል በላይ 3,192 ሜ. ከፍታ ላይ የሚገኝ ከመሆኑ አኳያ የውጤታማ አትሌቶች መገኛ ሊሆን ስለሚችል ሊደግፉትና ሊያጠናክሩ እንደሚገባቸው ተገልጿል።

በዚህ ካምፕ ሰልጥነው ሃገራችንን በአለም አደባባይ ስሟን ያስጠሩ ከ22 የማያንሱ ውጤታማ የሜዳልያ አትሌቶች ተገኝተዋል።

ከነዚህ መካከል፣
ሴቶች፣

አባበል የሻነህ፣
ዘርፌ ልመንህ፣
ስለናት ይስማው፣
እመቤት አንተነህ፣
ቢተው ይሁኔ፣
ማሬ ቢተው፣
ስንታዬሁ ጥላሁን፣
ስንታዬሁ ማስሬ፣
ካሱ ቢተው፣
መልካም ጥላሁን፣

ወንዶች፣

ፅዳት አበጀ፣
አምደወርቅ ዋለልኝ፣
ይግረም ደመላሽ፣
የኔው ጠብቀው፣
ለይኩን ብርሃኑ፣
ታዬ ብርሃኑ፣
መኩሪያው ዘለቀ፣
ንብረት መላክ፣
እንየው ንጋት፣
ታድሎ ጌጡ፣
አምሣሉ ቢረሳው፣
አይቶልኝ ካሣሁን ይጠቀሳሉ።

ፌዴሬሽኑ የካምፑን አጠቃላይ ገፅታ ከተመለከተ በኋላ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እንደሚያሟላም ፕሬዝዳንቷ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ በወቅቱ ለአመራሮቹ አስታውቃለች።

Similar Posts
Latest Posts from