35ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን በደማቅ ሁኔታ በባህርዳር ተከናውኗል።

ሰኔ 9/2011 ዓ. ም በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው በዚህ ውድድር፣

ከ50 በታች አንጋፋ አትሌቶች፣
1ኛ ገዛኸኝ ገብሬ፣
2ኛ በሪሁን ተስፋዬ፣
3ኛ ቶለሣ ገብሬ፣

ከ50 በላይ አንጋፋ አትሌቶች፣
1ኛ አያሌው እንዳለ፣
2ኛ ይበልጣል ቢያልፈው፣
3ኛ ተስፋዬ ጉታ፣

ማራቶን፣
በሴቶች፣
1ኛ አሸቴ በከሪ፣ ኦሮ/ፖሊስ፣ 2:30.60
2ኛ ዘይቱና አረባ፣ ፌዴ/ማረሚያ፣ 2:32.45
3ኛ መሠረት ድንቄ፣ በግል፣ 2:33.10

በወንድ፣
1ኛ ፍቅሬ በቀለ፣ ፌዴ/ፖሊስ፣ 2:11.04 የዋንጫ ተሸላሚ
2ኛ መኳንንት አየነው፣ ኢት/ን/ባንክ፣ 2:11.27
3ኛ ብርዬ ተሾመ፣ ፌዴ/ፖሊስ፣ 2:12.05

በቡድን፣
ወንድ፣
1ኛ ፌዴ/ፖሊስ፣ በ17 ነጥብ፣
2ኛ መከላከያ፣ በ40 ነጥብ፣
3ኛ ኢትዮ/ኤሌክትሪክ፣ በ72 ነጥብ፣

ሴት፣
1ኛ ፌዴ/ፖሊስ፣ በ37 ነጥብ፣ የዋንጫ ተሸላሚ፣
2ኛ ኦሮ/ፖሊስ፣ በ55 ነጥብ፣
3ኛ ፌዴ/ማረሚያ፣ በ58 ነጥብ፣

እዚሁ ውድድር ላይ ከ1974 ዓ. ም ጀምሮ ባለማቋረጥ ሲሳተፉ የቆዩት የ85 አመቱ አንጋፋ አትሌት፣ የመጀመሪያው የጎጃም ጠቅላይ ግዛት ሯጭ፣ ከ1965 ጀምሮ የአፍሪካ ምርጥ፣ በርካታ የአለምና የአፍሪካ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያን ወከለው የሮጡት አንጋፋ አትሌት ታደሠ ፀጥአርጋቸው በቅርቡ በተመሠረተው የኢትዮጵያ አንጋፋ አትሌቶች ማህበር የተዘጋጀላቸውን የ5,000 ብር ማበረታቻ ሽልማት ከኢአፌ ተቀ/ም/ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ እጅ የተረከቡ ሲሆን ሌሎች ግለሰቦችም ሸልመዋቸዋል።

Similar Posts
Latest Posts from