የማራቶን አትሌቶች ምርጫ፣

ግንቦት 21/2011 ዓ. ም. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ17ኛ ጊዜ በዶሃ ኳታር እ.ኤ.አ. ከሴፕቴምበር 27 – ኦክቶበር 6/2019 ዓ. ም. ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ሊወክሉ የሚችሉ የማራቶን ቡድን አትሌቶችን ከነተጠባባቂዎቻቸው መርጧል፡፡

አትሌቶቹ በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ዋና (Major) እና የወርቅ (Gold) ደረጃ በተሰጣቸው ማራቶኖች እ.ኤ.አ ከሴፕቴምበር 2018 – አፕሪል 2019 ድረስ ተወዳድረው ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት ሊመረጡ ችለዋል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

በወንዶች፣
1. አትሌት ሞስነት ገረመው፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡02.55
2. አትሌት ሙሌ ዋሲሁን፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡03.16
3. አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፤ 2018፣ ኒውዮርክ፣ 2፡05.59
4. አትሌት ሹራ ኪጣታ፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡05.01 ተጠባባቂ፣
5. አትሌት ብርሃኑ ለገሰ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡04.48 ተጠባባቂ፣
6. አትሌት ታምራት ቶላ፤ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡04.06 ተጠባባቂ፣

በሴቶች፣
1. አትሌት ሩቲ አጋ፣ 2018፣ በርሊን፣ 2፡18.34
2. አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ፣ 2019፣ ዱባይ፣ 2፡17.41
3. አትሌት ሮዛ ደረጀ፣ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡19.17
4. አትሌት ሹሬ ደምሴ፣ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.05 ተጠባባቂ፣
5. አትሌት ሄለን ቶላ፣ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.01 ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
የሰዓት ልዩነት የሚታየው በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ደረጃ አሰጣጥ መሰረት የማራቶኖቹ ደረጃ ስለሚለያይ መሆኑን እየገለፅን በምርጫው ቅሬታ ያለው አትሌት ካለ ቅሬታውን በጽሁፍ ለፌዴሬሽኑ እስከ ማክሰኞ ግንቦት 27/2011 ዓ. ም ድረስ ማቅረብ ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Similar Posts
Latest Posts from