የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኮት ዲቯር – አቢጃን በአፍሪካ ወጣቶችና ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ  ኢትዮጵያን ወክሎ በ6 የወርቅ፣ በ10 የብር፣ በ14 የነሃስ፣ በጠቅላላው 30 ሜዳልያ በማስመዝገብ በድል ወደ ሃገሩ የተመለሰውን የልዑካን ቡድን ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 14/2011 ዓ. ም. ማለዳ 3:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሆቴል የአቀባበልና የማበረታች የገንዘብ ሽልማት ፕሮግራም አካሂዷል። ፌዴሬሽኑ ለሽልማት ብቻ ብር 875,000.00 መመደቡም ይታወቃል።

ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በፕሬዝዳንቱ ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ አማካይነት ለቡድኑ አባላት በጥቅል ብር 450,000.00፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ሆቴል ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ በግላቸው ከብር 150,000.00 በላይ ለቡድኑ አባላት ሸልመዋል። ከዚህም ባለፈ የኢትዮጵያ ሆቴል የምሣ መስተንግዶውን ሙሉ በሙሉ በመሸፈን አስተናግዷል።

በአቀባበሉ ፕሮግራም ላይ የፌዴሬሽኑ ም/ፕሬዝደንት አትሌት ገ/እግዚአብሄር፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ዶ/ር አሸብርና የፌዴሬሽኑ ስፖንሰር ሄኒከን ኢትዮጵያ ሶፊ ማልት ምርት ተወካይ አቶ ፍቃዱን ጨምሮ በየተራ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በተያያዘ መረጃ የቡድኑ መሪ አቶ ፈሪድ መሃመድ በአቢጃን ቡድኑ ስለነበረው ቆይታ አብራርተዋል።

በስለሺ ብሥራት፣ የኢአፌ ኮሙኒኬሽን ከፍ/ ባለሙያ፣

Similar Posts
Latest Posts from