በሃገር ቤትም በውጪም ለምትኖሩ መላው የአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቦች፤

ጉዳዩ፡ ምስጋና ማቅረብን ይመለከታል፡፡

በቅርቡ በዴንማርክ – አርሁስ ከተማ ለ43ኛ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ በመካፈል ብሔራዊ አትሌቶቻችን በ5 ወርቅ፣ በ3 ብርና በ3 ነሃስ ሜዳልያዎች ከዓለምም ከአፍሪካም ቀዳሚ በመሆን ታሪክ ማስመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

ለዚህ ደማቅ ታሪክ እውን መሆን ደግሞ የሁላችሁም ሚናና አስተዋፅዖ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በፅኑ ያምናል፡፡

በመሆኑም በማንኛውም መልኩ ከጎናችን ሆናችሁ ስላበረታታችሁን፣ ሞራል ስለሆናችሁንና መልካም ስለተመኛችሁልን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስም ከልብ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን፡፡

ይህ አብሮነታችሁ ደግሞ ምንጊዜም እንደማይለየንና ሁሌም አብራችሁን እንደሆናችሁ ስንገነዘብ ሌላ ተጨማሪ አቅም ይሆነናልና ምን ጊዜም አብራችሁን ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ደራርቱ ቱሉ (ኮሎኔል አትሌት)
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት

Similar Posts
Latest Posts from