በ43ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው የልዑካን ቡድን  መጋቢት 16/2011 ዓ. ም ከምሽቱ 12:30 ሰዓት ጀምሮ በአራራት ሆቴል ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎለታል።

በርካታ ታዋቂና ስመ ጥር የቀድሞ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት፣ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሚዲያ አካላት በተገኙበት ቡድኑ ተሸኝቷል።

ክብርት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በመልካም ምኞት መግለጫዋ እንዳመለከተችው የአገር አቋራጭ ውድድር መገለጫችን በመሆኑ በ43ኛው ሻምፒዮናም ቡድኑ ውጤታማ ይሆናል ብላ እንደምታምን አስታውቃለች።

ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢኦኮ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ድጋፋችንን ከፍ እያደረግን ከፌዴሬሽኑ ጋር እንሰራለን ካሉ በኋላ ውጤታማ ስትሆኑ መንግስት ማበረታቻውን በሚሊዮኖች ሊያሳድግ እንደሚችል አረጋግጠዋል።

በዚህ ሥነ ስርዓት ላይ የሰንደቅ ዓላማ የአደራ ርክክብ የተደረገ ሲሆን ወንድና ሴት የአትሌቶች ተወካዮችና የአሰልጣኞች ተጠሪ ሁሴን ሽቦ የነበረውን የሥልጠና ዝግጅት አድንቀው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የጋራ የፎቶግራፍ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል።

በስለሺ ብሥራት፣ የኢአፌ ኮሙኒኬሽን ከፍ/ባለሙያ፣

 

 

Similar Posts
Latest Posts from