19ኛው የሜጀር ጄኔራል ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ 15 ኪ.ሜ. የጐዳና ላይ ሩጫ ውድድር ታህሳስ 08/2010 ዓ.ም. በድሬደዋ ከ/አስተዳደር ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

ዓላማ

የሜጀር ጄኔራል ኃየሎም አርአያ ተጋድሎ ታሪክ በየዓመቱ ለማሰብና ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች በ15 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በመካፈል ልምድ እንዲያካብቱ ለማድረግና ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት፤ እንዲሁም ለአትሌቶች የጐዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዕድል ለመፍጠር ነው፡፡

የምዝገባ ጊዜ

1. 19ኛው የሜጀር ጄኔራል ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ 15 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ምዝገባ ከህዳር 26 እስከ ታህሳስ 02/2010 ዓ.ም. ድረስ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት የተወዳዳሪዎችን ስም ዝርዝር በመላክ መመዝገብ ያስፈልጋል፡፡
2. በውድድሩ የምዝገባ ገደብ ውስጥ ያልተመዘገበ ክልል/ከተማ አተዳደርና ክለብ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ታህሳስ 03/2010 ዓ.ም. ብቻ መመዝገብ አለበት፡፡
3. ማንኛውም ተሳታፊ ክልል/ከተማ አስተዳደርና ክለብ በየፆታው ከሦስት እስከ ስድስት አትሌቶችን ማስመዝገብ ይችላል፡፡

ሽልማት

ለዚህ ውድድር ፌዴሬሽኑ በአጠቃላይ 100,000.00 ብር ለሽልማት መድቧል፡፡

Similar Posts
Latest Posts from