ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እሁድ የካቲት 3/2011 በ36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ዙሪያ ዛሬ ጥር 29/2011 ዓ. ም. ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢ አዳራሽ ለስፖርት ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በዚህ መግለጫ ወቅት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ የቴክኒክ ኃላፊው ክቡር አቶ ዱቤ ጅሎ ስለውድድሩ ሙሉ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
እንደ ክብርት ፕሬዝዳንቷ ገለፃ በ36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና
• ከ6 ያላነሱ አጋር የመንግስት መ/ቤት ኃላፊዎች፣
• የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣
• በርካታ ውጤታማ፣ ታዋቂና ስመ ጥር አትሌቶች፣
• የአትሌት ማናጀሮችና ተወካዮቻቸው፤
• ከተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ኃላፊዎች፣
• ሁሉም የስፖርት ሚዲያ ተቋማት፣ የጎረቤት አገራት አትሌቶች ተጋብዘውበታል፡፡
• ውድድሩ እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ በኢቲቪ መዝኛና ቻናል ከማለዳው 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለ3 ሰዓታት ያህል የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ ተንታኝ ታዋቂ አትሌቶች ውድድሮቹን እየተከታተሉ ትንተና ይሰጣሉ፡፡
• ከዚህ ውጪ ሻምፒዮናው ሃገራችን በ43ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ የሚያበቋትን ውጤታማ አትሌቶች የምንመርጥበት ትልቅ ሻምፒዮና ነው፤ ብለዋል፡፡
ከማብራሪያው በኋላ ከስፖርት ጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና

 • የውድድሩ ቀን፡- የካቲት 03/2011 ዓ.ም.
 • የውድድሩ ቦታ፡- ጃንሜዳ

የውድድሩ ዓላማ፡-

 • ክልሎችን፣ ከተማ አስተዳድሮችን፣ ክለቦችንና የአትሌቲክስ ማመሠልጠኛ ማዕከላት በኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍና ውጤታማ አትሌቶችን በመምረጥ እ.ኤ.አ. ማርች 30/2019 በዴንማርክ አርሁስ ከተማ በሚካሄደው 43ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ነው፡፡

የውድድሩ ተሳታፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ፡-

 • ክልሎች፣ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ማሰልጠኛ ማዕከላትና ተቋማት ሲሆኑ፤
 • ከውጭ ሃገራትም ከኤርትራ፣ ከሱዳን፣ ከጅቡቲ በሻምፒዮናው ላይ ይሳተፋሉ፤
 • በዚህ ውድድር ላይ ሰባት ክልሎች፣ ሁለት ከተማ አስተዳደር፣ ሰላሳ አምስት ክለቦችና ተቋማት፣ ቬትራንና በግል ተመዝግበው የሚወዳደሩ አትሌቶች ሲኖሩ፤
 • የተወዳዳሪ ብዛት 300 ሴት፣ 616 ወንድ በአጠቃላይ 916 አትሌቶች ለመወዳደር ተመዝግበዋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከሚሳተፉ ታዋቂ አትሌቶች መካከል፡-

በወንዶች

 • ጌታነህ ሞላ፣ ሙክታር እድሪስ፣ ኢማና መርጊያ፣አፀዱ ፀጋይ ከመከላከያ
 • ሃጎስ ገ/ሕይወት                              ከመስፍን ኢንጅነሪግ
 • ጀማል ይመር                              ከአማራ ማረሚያ
 • አንዱአምላክ በልሁ                             ከሲዳማ ቡና
 • ሚልኬሳ መንገሻ፣ ጅግሳ ቶሎሳ ከኦሮሚያ ክልል
 • ሞገስ ጥዑማይ                            ከመሰቦ
 • አባዲ ሀዲስ                            ከትራንስ ኢትዮጵያ
 • ማስረሻ በሬ                            ከፌዴ/ማረሚያ
 • ሞስነት ገረመው                             ከአማራ ፖሊስ
 • ይከበር ባያብል፣ ሰለሞን ዴክሲሳ ከኢት/ንግድ ባንክ

በሴቶች

 • ማሚቱ ዳስካ፣ፈይኔ ጉደቶ  ከኦሮሚያ ፖሊስ
 • ሰንበሬ ተፈሪ ከፌዴ/ማረሚያ
 • ብርቱካን ፈንቴ፣ አዝመራ ገብሩ፣ ብርቱካን አዳሙ ከኢት/ኤሌትሪክ
 • በሱ ሳዶ                                   ከአዳማ ከተማ
 • ፎቴን ተስፋዬ ከመሰቦ
 • ሀዊ ፈይሣ፣ ዘርፌ ልመንህ፣ ሽቶ ውዴሣ ከመከላከያ
 • ለተሰንበት ግደይ ከትራንስ ኢትዮጵያ
 • ሕይወት አያሌው፣ ገነት ጋሽዬ ከኢት/ንግድ ባንክ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የ36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ተወዳዳሪ አትሌቶች ብዛት (ዳታ)

ተ.ቁ ክልል፣ከ/አስተዳደር ክለብ፣ተቋምና ማዕከላት የውድድር ካታጎሪ
ከ20 ዓመት በታች አዋቂ ድብልቅ(Mixed Relay)  

ድምር

6 ኪ.ሜ

ሴት

8 ኪ.ሜ  ወንድ 10 ኪ.ሜ

ሴት

10 ኪ.ሜ

ወንድ

8 ኪ.ሜ

  ወ/ሴ

1. አማራ ፖሊስ 4 2 4 6 16
2. ሀበሻ አትሌቲክስ 4 4 2 5 15
3. ኢትዮጵያ ኤሌትሪክ 11 8 7 6 4 36
4. ርሆቦት አትሌቲክስ 8 12 20
5. ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት 2 4 6
6. ፌደራል ማረሚያ 8 12 4 24
7. ዱከም ከተማ 6 6
8. ጌታ ዘሩ 10 12 3 8 33
9. ትራንስ ኢትዮጵያ 8 6 3 5 22
10. አማራ ክልል 10 12 11 10 4 47
11. አማራ ማረሚያ 1 2 1 5 9
12. መድሃኒዓለም አትሌቲክስ 4 6 2 4 16
13. ጉና ንግድ ሥራዎች 6 6 12
14. ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 5 5 13
15. መከላከያ 5 10 7 12 4 38
16. ደብረ ብረሃን ማሰልጠኛ ማዕከል 2 2 1 5
17. መስፍን ኢንደስትሪያል 2 2 5 9
18. ደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ 2 5 7
19. ጥሩነሽ ዲባባ 5 12 1 4 22
20. ሱር ኮንስትራክሽን 4 5 1 4 4 18
21. ፌደራል ፖሊስ 6 12 12 30
22. ኦሮሚያ ፖሊስ 10 12 12 12 4 50
23. መሶቦ ሲሚንቶ 1 2 1 4 4 12
24. ድሬደዋ ከተ/አስተዳደር 2 3 5
25. አዳማ ከተማ 5 2 4 11
26. ኦሮሚያ ክልል 12 11 11 11 4 49
27. ብርሃንና ሰላም 3 1 4 8
28. ኦሮሚያ መንገዶች ኮንስትራክሽን 3 3 4 10
29. ኢትዮጵያ ተገን 2 8 2 12
30. ሀረሪ ክልል 3 5 8
31. ኮስሞ ኢንጂነሪንግ 4 4
32. ኢት/ኮን/ስራዎች ኮርፖሬሽን 3 2 4 9
33. ሲዳማ ቡና 4 4 8
34. ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች 4 4 8
35. አዲስ አባባ ከተ/አስተዳደር 1 1 4 6
36. ራን አፍሪካ አትሌቲክስ 2 6 8 16
37. አፋር ክልል 6 6
38. ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት 4 4
39. ደቡብ ክልል 5 8 8 21
40. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 8 1 11 12 4 36
41. ሃዋሳ ከነማ 7 7 3 5 4 26
42. ትግራይ ፖሊስ 4 1 2 3 10
43. የኢትዮጵያ ሱማሌ 1 5 2 8
44. የኢት/ወጣቶች ስፖ/አካዳሚ 4 9 13
45. አዲስ አበባ አንጋፋ ከ50 በላይ 19 19
46. አዲስ አበባ አንጋፋ ከ50 በታች 15 15
47. የግል 4 19 5 110 138
አጠቃላይ ድምር 155 267 113 317 64 916

Similar Posts
Latest Posts from