5ኛው የ30 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ

ለ5ኛ ጊዜ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ የ30 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ታህሳስ 7/2011 ዓ.ም. በሁለቱም ፆታ እንዲሁም አንጋፋ አትሌቶችን ጨምሮ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ላይ ከ3 ክልሎች፣ ከ2 ከተማ አስተዳድሮች፣ ከ12 ክለቦችና ተቋማት፣ በግል ተመዝግበው የሚደዳደሩና አንጋፋ አትሌቶችን አካቶ 98 ሴቶች እና 335 ወንዶች በድምሩ 423 አትሌቶች ተካፍለውበታል፡፡

ውድድሩ ከማለዳው  1:25 ሰዓት  በሴቶችና በአንጋፋ (ቬትራን) አትሌቶች ምድብ የተጀመረ ይህው ውድድሩ ከተጀመረ ከ20 ደቂቃ በኋላ የወንዶቹ  ውድድር  የተጀመረ ሲሆን የፌዴሬሽናችን ፕሬዝዳንት ኮ/ሌ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ውድድሮቹን አስጀምራለች፡፡

ከአትሌቶች ሽልማት ቀደም ብሎ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ህልፈት አስመልክቶ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡

ቢሾፍቱ ሰርክል አደባባይ ፍጻሜውን ባደረገው ሻምፒዮና፡-

በአንጋፋ (ቬትራን) አትሌቶች የ15 ኪ.ሜ አሸናፊዎች
50 ዓመት በላይ

1ኛ አያሌው እንዳለ
2ኛ ካሱ መርጊያ
3ኛ ተስፋዬ ጉታ

4ኛ ይበልጣል ቢያልፈው

50 ዓመት በታች

1ኛ ገዛኸኝ ገብሬ
2ኛ ዳንኤል ቄቤሎ
3ኛ ንጋቱ አጋ

4ኛ ምናለ መኮንን ሆነው አጠናቀዋል።

30 ኪሜ የሴቶች ወድድር የግል አሸናፊዎች፡-

1ኛ ሮዛ ደረጄ ከፌዴራል ማረሚያ 1:46፡33
2ኛ ታደለች በቀለ ከኦሮሚያ ማረሚያ 1:46፡44
3ኛ ዝናሽ መኮንን ከኦሮሚያ ፖሊስ 1:46፡53

4ኛ መሰረት ድንቄ በግል 1፡47፡32

5ኛ ሂሩት ጥበቡ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡48፡05

6ኛ መሰረት ጎላ ከፌደራል ፖሊስ 1፡48፡16

7ኛ ኦብሴ አብደታ ከኦሮሚያ ክልል 1፡48፡39

8ኛ ዓለም ፀጋዬ በግል 1፡49፡13

9ኛ መገርቱ አለሙ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡49፡33

10ኛ ሹሬ ደምሴ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡50፡08

በሴቶች የቡድን አሸናፊዎች

1ኛ ኦሮሚያ ፖሊሰ በ27 ነጥብ ዋንጫ ተሸላሚ
2ኛ ፌዴራል ፖሊሰ በ52 ነጥብ
3ኛ ኦሮሚያ ማረሚያ በ57 ነጥብ

30 ኪሜወንዶች ወድድር የግል አሸናፊዎች፡-

1ኛ ፅዳት አበጀ ከኢት/ኤሌክትሪክ 1:31፡56
2ኛ ጅግሳ ታደሰ ከኦሮሚያ ክልል 1:32፡06
3ኛ ፍቅረ በቀለ ከፌዴራል ፖሊስ 1:32፡09

4ኛ አሰፋ ተፈራ ከሀዋሳ ከነማ 1፡32፡16

5ኛ አዱኛ ታከለ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡32፡47

6ኛ ብርሃኑ በቀለ ከኦሮሚያ ፖሊስ 1፡33፡25

7ኛ ልመንህ ጌታቸው ከመከላከያ 1፡33፡46

8ኛ ባንተእድል ይታየው ከመከላከያ 1፡34፡02

9ኛ ሂርቦ ሻኖ ከደቡብ ፖሊስ 1፡34፡19

10ኛ ሃይማኖት ማተብ ከጌታ ዘሩ 1፡34፡37

በወንዶች የቡድን አሸናፊዎች

1ኛ ፌዴራል ፖሊስ በ64 ነጥብ
2ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ በ70 ነጥብ
3ኛ መከላከያ በ70 ነጥብ አሸናፊ ሆነዋል።

ለአሸናፊ አትሌቶች ከሜዳልያ በተጨማሪ በሁለቱም ፆታ ከ1ኛ አስከ 10ኛ ለወጡ አትሌቶች ከ30,000 እስከ 2,000 ብር እንዲሁም ለአንጋፋ አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ለወጡ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ በአጠቃላይ 250 ሺ ብር ለአሸናፊ አትሌቶች የሸለመ ሲሆን በቡድንና በግል አሸናፊ ለነበሩ ቡድኖችና አትሌቶች የዋንጫ የሜዳልያና ሽልማት አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱ በደማቅ ሁኔታ በእለቱ የክብር እንግዶች ተከናውኖ ውድድሩ ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ ተጠናቋል።

በስለሺ ብሥራት – የኢአፌ ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ፤

Similar Posts
Latest Posts from