ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ሲጀምር በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሃብታሙ ሲሳይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመልእክታቸውም መንግስት ስፖርት ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ህብረተሰቡ በሚኖርበት በሚሰራበትና በሚማርበት አከባቢዎች ታሳተፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት መሰራት እንደሚገባው ያስገነዘቡ ሲሆን ለዚህም ተግባራዊነት ከምን ጊዜውም በበለጠ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ገፀዋል፡፡ በተለይም አትሌቲክስ የሀገራችን መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ፌዴሬሽኑ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳሰቡ ሲሆን በአንዳንድ የስፖርት አይነቶች ላይ የሚታዩት የስነምግባር መርሆዎች መጣስ እንዲሁም የአበረታች ቅመሞችን መጠቀም በተመለከተ የስፖርቱ ማህበረሰብ አጥብቆ ሊያወግዘው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሄኒከን ኢትዮጵያ ስፖርቱን በዘላቂነት እንደሚደግፍ የጠቀሱ ሲሆን በተለይም በሶፊ ማልት ብራንዳቸው አትሌቲክስን መደገፍ እንደሚቀጥሉ የሶፊ ማልት ተወካይ አቶ ፈቃዱ ባሻ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም የኢ.አ.ፌ ፕሬዝዳት ሻ/ቃ አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ የመግቢያ ንግግርና አጭር የ2009ዓ.ም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ ከአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ስቴፈን በርሞን አትዮጵያ የአትሌቶች የእድሜ ተገቢነት ችግርና የአትሌቶች ጤና ላይ አትኩሮ አንዲሰራ አስገንዝበዋል፡፡

 

በከሰዓት በኋላ ውሎውም ጉባኤው የ2010 በጀት አመት የኦዲት ሪፖርት ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡ በመቀጠልም የፌዴሬሽኑን የ2011 በጀት ዓመት የስራ እቅድ ላይ የተወያየ ሲሆን የበጀት ዐመቱን የትኩረት አቅጣጫዎችም በእቅዱ አመላክቷል

 

የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፡-

  • በሰንዳፋ በኬ እና በአትሌቲክስ ስፖርት ጂምና የህክምና ማዕከል ለማስገንባት ያስችል ዘንድ የቦታውን ችግር ለመፍታት ግብረ-ኃይል ማቋቋም እና ጠንከር ያለ ክትትል በማድረግ ችግሩን በመፍታት ግንባታውን ማስጀመር፣
  • በየደረጃው የሚገኙ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን፣በመጠገን እና በመጥረግ ለስልጠና አገልግሎት እንዲውሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመደጋገፍና በመተባበር መስራት፣
  • ለውድድር አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን(ፎቶ ፍኒሺንግ፣ ሌሎች መሣሪያዎች) በማሟላት የውድድር ስታንዳርዱን ማሳደግ ፣
  • 4ቱን የስልጠና ማዕከላት በሰው ኃይል፣ በግብዓት እና በሙያ ማጠናከርና የተጀመረውን የተተኪ ማፍራት ስራቸው ውጤታማ ማድረግ፤
  • ለአህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ውድድር ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ተገቢውን ጊዜና በጀት በመመደብ ውጤት ሊያስመዘግብ የሚችል ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል ፣
  • በአትሌቶች የሚታዩ የዕድሜ ችግር፣ የማናጀሮች በአትሌቶች ላይ የሚያሳዩትን የውድድር ጫናና ሌሎች ችግሮችን ሊያስተካክል የሚችል ህግና ደንብ በማውጣት በትክክል መተግበር፣
  • የፀረ-አበረታች ቅመም (ዶፒንግ) እንቅስቃሴን በግንዛቤና በምርመራ አጠናክሮ መቀጠል፣ የሚሉት ዋናዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ይሆናሉ በቀረበው እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ የተሰጡት ግብአቶች የሚካተቱበት ሆኖ እቅዱ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

22ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ማምሻውን ሲቀጥል፤ በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ የአባላት ጥንቅርና የክለቦች ተሳትፎ ጉዳይ ላይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ ወቅት የአሰልጣኞች ማህበር በስራ አስፈፃሚኮሚቴ ውስጥ ይካተት የሚል ሃሳብ የተነሳ ሲሆን ከ አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አደረጃጀት ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ሀሳቡ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ በተጨማሪም የክለቦች የጠቅላላ ጉባኤ አባልነት ከሚሳተፉት ተጨማሪ አባላት ይካተቱ በሚል ውይይት የተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ሃሳብ ይዞ ስራ አስፈፃሚው እንዲመጣ ለሌላ ጉባኤ ተላልፏል፡፡

 

በመጨረሻም ጉባኤው የተዘጋጀውን የአትሌቲክስ የስልጠና ማስዋል በማስመረቅ እንዲሁም በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳድሮችና ክለቦችን በመሸለም አጠናቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ለክልሎች
1ኛ የኦሮሚያ ብሄራዊ መንግስት አተሌቲክስ ፌዴሬሽን —–ብር 240,000
2ኛ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን—–ብር 180,000
3ኛ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልላዊ መንግሰት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን—–ብር 140,000
3ኛ የአዲስ አበባ ከ/እተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ————ብር 140,000
5ኛ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን——ብር 80,000
6ኛ የሀረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን——– ብር 60,000
7ኛ የቤኒሻንጉልጉምዝ ክልላዊ መንግሰት አትሌቲክስ ፌዴሬሽን– ብር 40,000
8ኛ የድሬደዋ ከ/አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን—————-ብር 20,000

ለክለብ

1ኛ መከላከያ አትሌቲክስ ስፖርት ክለብ—–ብር 300,000
2ኛ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ—-ብር 240,00
3ኛ የኢት/ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ስፖርተ ክለብ—ብር 180,00
4ኛ የኦሮሚያ ስፖርት ክለብ——ብር 140,000
5ኛ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ—- ብር 100,000
6ኛ የፌደራል ፖሊስ ስፖርት ክለብ——–ብር 80,000
7ኛ የሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ስፖርት ክለብ—ብር 60,000
8ኛ ጥሩነሽ ዲባባ ብ/አት ማሰልጠኛ ማእክል —ብር 40,000

Similar Posts
Latest Posts from