በፊንላንድ ታምፔ ሬ ነገ እሮብ ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚጀመረው 17ኛው የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሃገራችንን የሚወክለው ቡድናችን ዛሬም በማለዳ ለ2ኛ ቀን ቀለል ያለ ልምምድ የሰራ ሲሆን በነገው እለት ማለዳ 3፡30 ሰዓት ላይ በሴቶች 3,000 ሜ. መሰናክል፣ 4፡05 ሰዓት ላይ በሴቶች 1,500 ሜ. ፣ 4:40 ላይ በሴቶች 800 ሜ. ማጣሪያ ውድድሮችን እናደርጋለን።

ከሰዓት በኋላ በሴቶች 400 ሜ. ማጣሪያና 5,000 ሜ. ሴቶች፣ 10,000 ሜ. ወንዶች የፍፃሜ ውድድሮችን እናደርጋለን።

የታምፔሬ ሰዓት አቆጣጠር ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ነው።

ድል ለአትሌቶቻችን!!!

Similar Posts
Latest Posts from