ቤተሰቦቻቸው፣ የኢፌዲሪ ወ/ስ/ሚ/ር፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ በመሆን ያሰሩት የጀግናው ማርሽ ቀያሪ አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠርና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ መሐንዲስ ተብለው የሚጠሩት ዋና አሰልጣኝ ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ የመቃብር ላይ ሐውልት የወ/ስ/ሚ/ር ሚኒስትር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ የሶስቱ ተቋማት ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በተገኙበት በፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ታጅቦ በታላቅ ሥነ ስርአት ሚያዝያ 28/2010 ዓ. ም. ከማለዳው 4፡30 ሰዓት ላይ ተመርቋል፡፡

         

 

 

 

 

 

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤ/ክ ቀሳውስት፣ ካህናትና ዲያቆናት ፍትሐተ ጸሎት ካደረጉ በኋላ የሁለቱም ጀግኖች የህይወት ታሪክ በንባብ ተሰምቷል፤ ቤተሰቦቻቸው ባደረጉት የምስጋና ንግግርም ከጎናቸው ለነበሩትና በምክርም በልዩ ልዩ ድጋፍም ላልተለዩዋቸው ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

በመቀጠልም የሶስቱ ተቋማት ኃላፊዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን አገራቸውን በአለም አደባባይ ያስጠሩ ጀግኖች አትሌቶችን ከመቃብር በታች ሲውሉ ሳይሆን በህይወት እያሉ ጭምር ማስታወስና መደገፍ እንደሚገባ በመልእክታቸው አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም የሁለቱ ጀግኖች ሃውልቶች በቤተሰቦቻቸውና በሶስቱም ተቋማት ኃላፊዎች ተመርቀዋል፡፡

      

ስለሺ ብሥራት – የኢአፌ ህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ፤

Similar Posts
Latest Posts from