የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለስድስተኛ ጊዜ ከግንቦት 15 – 19/2010 ዓ. ም. ለ5 ቀናት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አሰላ ከተማ አረንጓዴው ስቴድዮም በድምቀት ይካሄዳል፡፡

የዚህ ሻምፒዮና አላማ ደግሞ በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮችና በክለቦች ውስጥ ለሚገኙ ወጣት አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እና እ.ኤ.አ ከጁላይ 10 – 15/2018 ዓ. ም. ፊንላንድ ቴምፔሬ  በሚደረገው የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክለው  የሚሳተፉ  አትሌቶችን ለመምረጥ ነው፡፡

በ6ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ የክልል፣ የከተማ አስተዳድር፣ የክለብ፣ የጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከልና የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ እና ተቋማት ተወዳዳሪ አትሌቶች ይሆናሉ፡፡

በውድድሩ ከአጭር ርቀት ጀምሮ የሜዳ ተግባራት፣ የመካከለኛና የረጅም ርቀት ሩጫዎች፣ የእርምጃ ውድድሮች የሚካተቱ ሲሆን ከ40 የማያንሱ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

ስለሺ ብሥራት – በኢአፌ የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ፤

Similar Posts
Latest Posts from