የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ

ለ6 ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ስቴድዮም ሲካሄድ የሰነበተው 47ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እሁድ ሚያዝያ 14/2010 ዓ. ም ከምሽቱ 2፡00 ሰኣት ላይ በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል፡፡

በዚህ ሻምፒዮና ላይ በርካታ ሪከርዶች ተሻሽለዋል፤ በርካታ አትሌቶች ባደረጓቸው 2 እና ከ2 በላይ ውድድሮች 2 እና ከ2 በላይ ሜዳልዎችን ማግኘት ችለዋል፡፡ ለዚህ ልፋታቸውና ውጤታቸው ደግሞየኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

በመዝጊያው ሥነ ስርአት ወቅት ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ባሰማው ንግግር ከዚህ የበለጠ አቅም እንዳላቸው ያስመሰከሩ አትሌቶችን ማየት መቻሉንና ገና አሁንም ብዙ መስራትና መጣር እንደሚገባ አሳስቧል፡፡  በንግግሩ ማጠቃለያ ላይም ከፍ ያለ ድጋፍና ጥረት ከታከለበት የዛሬው የአትሌቶቻችን ውጤት ለዓለም ስጋት የሚሆኑ ብርቱ አትሌቶች እናዳሉን ማሳያ ነው ብሏል፡፡

ለዚህ ውድድር መሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ከፍተኛ ምስጋናውን አቅርቦ የአትሌቲክስ ስፖርት በጋራ ርብርብ ለውጤት የሚበቃ ስፖርት መሆኑንንም አክሎ ገልጧል፡፡

የሁለቱም ጾታ አጠቃላይ ዋንጫ አሸናፊዎች፤

በሴቶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣

1ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ በ158 ነጥብ ዋንጫ ተሸላሚ፣

2ኛ. ኦሮሚያ ክልል፣ በ148 ነጥብ፣

3ኛ. ኢት/ንግድ ባንክ፣ በ107 ነጥብ፣

በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊዎች፣

1ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ፣ በ180 ነጥብ፣ ዋንጫ ተሸላሚ

2ኛ. ኦሮሚያ ክልል፣ በ177 ነጥብ፣

3ኛ. ሲዳማ ቡና፣ በ106 ነጥብ፣

በሁለቱም ጾታ አጠቃላይ አሸናፊዎች፣

1ኛ. መከላከያ ስፖርት ክለብ፣ በ338 ነጥብ ዋንጫ ተሸላሚ፣

2ኛ. ኦሮሚያ ክልል በ325 ነጥብ፣

3ኛ. ሲዳማ ቡና በ202 ነጥብ አሸንፈዋል፡፡

ስለሺ ብሥራት – በኢአፌ የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ኤክስፐርት፣

Similar Posts
Latest Posts from