ማለዳ ላይ መነሻና መድረሻውን አዲስ አበባ፣ 6 ኪሎ ያሬድ ሙዚቃ ት/ቤት ፊት ለፊት ያደረገው የወንዶችና ሴቶች 20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር በርካታ ተመልካች በተገኘበት በድምቀት ተካሂዷል፡፡

በውጤቱ መሰረት፡-

በሴቶች፤

1ኛ. የኋልዬ በለጠው፣  ከፌደራል ማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ በ1፡35.14

2ኛ. አይናለም እሸቱ፣  ከፌደራል ማረሚያ  ቤት ስፖርት ክለብ በ1፡40.41

3ኛ. ቤዛ ብርሃኑ፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ በ1፡44.52

በወንዶች፤

1ኛ. ዮሐንስ አልጋው፣ ከፌዴራል ማረሚያ  ስፖርት ክለብ በ1፡26.16

2ኛ. ቢራራ አለም፣  ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ክለብ በ1፡27.16

3ኛ. ታድሎ ጌጡ፣ ከአማራ ክልል በ1፡28.37 ሰዓት ውድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

የመዶሻ ውርወራ ወንዶች አሸናፊዎች፣

1ኛ. ብሩክ አብርሃም፣ ከኦሮሚያ ክልል፣ 46.73 ሜ.

2ኛ. አብርሃም ቶንጮ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ 45.35 ሜ.

3ኛ. ወርቁ ቶማ፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፣ 42.66 በሆነ ርቀት አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

የምርኩዝ ዝላይ ወንዶች አሸናፊዎች፣

1ኛ. ሳምሶን በሻህ፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፣ 4.41 ሜ. (የሻምፒ. ሪከርድ)

2ኛ. መዝገቡ ቢራራ፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፣ 4.20 ሜ.

3ኛ. ተከተል ታደሰ፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፣ 3.70 ሜ. በሆነ ከፍታ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

  

በርዝመት ዝላይ ወንዶች አሸናፊዎች፤

1ኛ. አዲር ጉር፣ ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፣ 7.31 ሜ.

2ኛ. ኡመድ ኡኩኝ፣ ከጥሩነሽ ዲባባ አት/ማሰ/ማእከል፣ 7.31 ሜ.

3ኛ. በቀለ ጅሎ፣ ከኦሮሚያ ክልል፣ 7.30 ሜ. በሆነ ርቀት አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

በሴቶች 400 ሜ. ውድድር አሸናፊዎች፣

1ኛ. ፍሬህይወት ወንዴ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ 53.34

2ኛ. ወርቅነሽ መለሰ፣ ከሲዳማ ቡና፣ 53.97

3ኛ. ፍሬዘውድ ተስፋዬ፣ ከኦሮሚያ ክልል፣ 54.35 በሆነ ጊዜ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ስለሺ ብሥራት – በኢአፌ የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ኤክስፐርት

Similar Posts
Latest Posts from