በሻምፒዮናው መክፈቻ ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የመክፈቻ ንግግር ያደረገ ሲሆን ከፕሬዝዳንቱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ጋር ም/ተ/ፕሬዝዳንቷ ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉና ም/ፕሬዝዳንቱ አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም በጋራ በመሆን የሻምፒዮናውን በይፋ መጀመር አስመልክተው በጋራ ርችት ለኩሰዋል፡፡

በ47ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያው ቀን የከሰዓት በኋላ መክፈቻ የሴቶች 10,000 ሜትር ውድድር እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የነበረበትና ተመልካቹን ቁጭ ብድግ ያስደርግ የነበረ ውድድር ሲሆን ውጤቱ እንደሚከተለው ሆኗል፤

1ኛ. ሃፍታምነሽ ተስፋይ – ከመከላከያ ስፖርት ክለብ በ33፡28.46

2ኛ. አስናቀች አወቀ – ከአማራ ማረሚያ ስፖርት ክለብ በ33፡30.91

3ኛ. ጌጤ አለማዬሁ – ከኦሮሚያ ውሃ ሥራዎች ስፖርት ክለብ በ33፡31.26 አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

           

በወንዶች መካከል በተካሄደ አስደናቂ የ10,000 ሜትር ውድድርም፤

1ኛ. ታዬ ግርማ – ከኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ስፖርት ክለብ  በ28፡26.68

2ኛ. አንዱአምላክ በልሁ – ከሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ  በ28፡29.68

3ኛ. ጀማል ይመር – ከአማራ ማረሚያ ስፖርት ክለብ 28፡30.22 በማስመዝገብ አሸንፈዋል፡፡

ሱሉስ ዝላይ የሴቶች ፍፃሜውን ያገኘ ውድድር ነው፡፡ በዚህ ውድድርም፤

1ኛ. አርያት ዲቦ – ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 12.72 ሜትር በመዝለል፤

2ኛ. ኡጁዳ ኡመድ – ከመከላከያ ስፖርት ክለብ 12.30 ሜትር፣

3ኛ. ነፃነት ኦብሴ – ከመከላከያ ስፖርት ክለብ 11.92 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 

ሌላው በዛሬው እለት የከፍታ ዝላይ ወንዶች ፍፃሜውን ያገኘ ውድድር ነው፡፡

                      

በዚህ ውድድርም፤

1ኛ. ዱፕ ሌም – ከሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ 2.01 ሜትር በመዝለል፤

2ኛ. አዲር ጉር – ከመከላከያ ስፖርት ክለብ 1.98 ሜትር፣

3ኛ. ገመቹ ታምሩ – ከመከላከያ ስፖርት ክለብ 1.95 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ስለሺ ብሥራት – በኢአፌ የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ኤክስፐርት

Similar Posts
Latest Posts from