ዓርብ ሚያዝያ 5/2010 ዓ. ም. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያና የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ ዱቤ ጅሎ ማክሰኞ ሚያዝያ 9/2010 የሚጀምረውን ውድድር አስመልክተው  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

    በመግለጫው ወቅት የተነሱ ዝርዝር ጉዳዮችም ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መረጃዎች፤

 • ሻምፒዮናው ለ47 ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ ነው፤
 • ሻምፒዮናው በአዲስ አበባ ስቴድዮም ከሚያዝያ 9 – 14/2010 ዓ. ም. ለ6 ቀናት ይካሄዳል፤

የሻምፒዮናው ዓላማ፤

 • በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮች፣ በክለቦች፣ በማሠልጠኛ ማዕከላትና ተቋማት ለሚገኙ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤
 • ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤
 • ለአህጉርና አለም አቀፋዊ አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች አገራችንን ወክለው የሚወዳደሩ፤ በተለይም ከኦገስት 1 – 5/2018 ለ22ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጤታማ አትሌቶችን ለመምረጥ፤

የተሳታፊ አካላት መግለጫ፤
9 ክልሎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች፣

 • ከ40 በላይ የአዲስ አበባና የክልል ክለቦች፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ ተቋማት፤

የዚህ ሻምፒዮና ልዩ መረጃዎች፤
ለዚህ ሻምፒዮና የተያዘ በጀት 1 ሚሊዮን ብር በላይ፣ /ካለፈው አመት አንፃር ሲተያይ በግማሽ እጥፍ ጨምሯል፤ 1.6 ሚ./

 • ታዋቂ አትሌቶች ሙሉ ለሙሉ ይሳተፋሉ፤ እንዲሁምስመ ጥር አትሌቶች በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፤
 • ለሽልማት 930,000.00 ብር በላይ በጀት ተይዟል፤ /100 ፐርሰንት ጨምሯል/
 • የሻምፒዮናውን ሪከርድ ለሚሰብሩ፣ በግል 2 እና ከዚ በላይ የወርቅ ሜዳልያ ለሚያመጡ አትሌቶች ልዩ ሽልማት ተዘጋጅቷል፤
 • በኢቴቪ መክፈቻውና መዝጊያው ለ3፡30 ሰዓት ያህል የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል፤
 • ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በክብር እንግድነትና በእንግድነት ተጋብዘዋል፣
 • ውድድሩን ለማካሄድ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከ280 በላይ ልዩ ልዩ ባለሙያዎችና 80 የአትሌቲክስ ዳኞች ተሳታፊ ይሆናሉ፣
 • በወንዶችና በሴቶች 42 የውድድር አይነቶች ይከናወናሉ፣
 • 100 . ጀምሮ እስከ 10,000 .፣ 3,000 . መሰናክል፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራትን በሙሉ ያካትታል፣

ተሳትፎ

 • ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች፡- 11
 • ክለቦች፡- ከ40 በላይ
 • ተሳታፊ አትሌቶች፡-
 • ወንድ 737
 • ሴት 500
 • ድምር 1,237

በዚህ ሻምፒዮና ላይ ይሳረፋሉ ተብለው የሚጠበቁ ታዋቂ አትሌቶች፤

 1. ኢማና መርጊያ         መከላከያ
 2. ሙክታር እድሪስ     መከላከያ
 3. ጌታነህ ሞላ            መከላከያ
 4. ሩቲ አጋ                 ፌዴ/ማረሚያ
 5. ሰለሞን ባረጋ           ደ/ፖሊስ
 6. አማን ወጤ             ኦሮ/ፖሊስ
 7. አባዲ ሃዲስ             ትራንስ
 8. ጉዳፍ ፀጋዬ              ሱር
 9. ሃብታም አለሙ         ኢት/ኤሌትሪክ
 10. በላይነሽ ኦልጅራ        ኢት/ንግ/ባንክ
 11. ልዑል ገ/ስላሴ          ኢት/ንግ/ባንክ
 12. ኮሬ ቶላ                   ኦሮሚያ ክልል
 13. ጫልቱ ሹሚ             ኦሮሚያ ክልል
 14. ድንቄ ፈርዴሳ            ኦሮሚያ ክልል
 15. በሱ ሳዶ                    ኦሮሚያ ክልል
 16. አንዱአምላክ በልሁ      ሲዳማ ቡና
 17. መሀመድ አማን           ሙገር
 18. አምደወርቅ ዋለልኝ      አማራ ክልል
Similar Posts
Latest Posts from