ቅዳሜ መጋቢት 15/2010 ዓ. ም. በስፔን ቫሌንሽያ በተካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያ በሴቶች በአትሌት ነፃነት ጉደታና በቡድን በሴቶችም በወንዶችም በአጠቃላይ ሶስት የወርቅ ሜዳልያዎችን በማግኘት ከአለምም ከአፍሪካም 1ኛ ደረጃ በመያዝ ሻምፒዮናውን አጠናቃለች፡፡


አትሌት ነፃነት ጉደታ 1፡06.11 በሆነ ጊዜ የዓለም ግማሽ ማራቶን የሴቶቹን ሪከርድ በመስበር ጭምር ነው ያሸኘፈችው፤ ለዚህም በውድድሩ አዘጋጅ  የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆን ችላለች፡፡


አትሌት ዘይነባ ይመር፣ መሰረት በለጠ፣ በቀለች ጉደታ የዲፕሎማ ባለቤቶች መሆን ችለዋል፡፡

በወንዶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ አትሌት ጀማል ይመር፣ ጌታነህ ሞላ፣ በተስፋ ጌታሁን የዲፕሎማ ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡

በስለሺ ብሥራት – የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ኤክስፐርት

Similar Posts
Latest Posts from