ከ3 ቀናት በኋላ ከማርች 1-4/2018 በእንግሊዟ በርሚንግሃም የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይካሄዳል፡፡ በዚህ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን የሚወክለው የአትሌቶች ቡድን ዛሬ ሰኞ የካቲት 19/2010 ዓ. ም. ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ወደ ስፍራው ይጓዛል፡፡ ኢትዮጵያ በ5 የውድድር አይነቶች በወንዶችና በሴቶች ተካፋይ ትሆናለች፡፡ በዚህ ቡድን ውስጥ ከተካተቱትና ወደ ስፍራው ከሚያቀኑት መካከል በየውድድር አይነቶቻቸው ሲታዩ፡-
በ800 ሜ. ሴቶች
ሐብታም አለሙ፣
በ1,500 ሜ ሴቶች
ገንዘቤ ዲባባ፣
ዳዊት ሥዩም፣
በ1,500 ሜ ወንዶች
ሳሙኤል ተፈራ፣
አማን ወጤ፣
በ3,000 ሜ. ሴቶች
ገንዘቤ ዲባባ፣
ፋንቱ ወርቁ፣
በ3,000 ሜ. ወንዶች
ሰለሞን ባረጋ፣
ሃጎስ ገ/ህይወት፣
ዮሚፍ ቀጀልቻ ሃገራችንን ይወክላሉ፡፡
ድል ለቡድናችን ተመኘን፡፡