ትናንት በተደረገው በጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ በእቅዱ መሠረት ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት መሰራታችን ጉልህ ሚና ነበረው።
አትሌቲክሱን ለማሳደግ እያንዳንዱ አካል የራሱን አስተዋጽኦ ማስቀመጥ እንደሚገባው እና በጋራ ከሰራን የማንሻገረው ፈተና እንደማይኖር የተመለከትንበት ውድድር ሆኖ አልፏል ።
ይህ እንዲሆን ደግሞ የውድድሩ ዋነኛ ባለቤት የሆኑት አትሌቶች፣ አሰልጣኞች ፤ የማሰልጠኛ ተቋማት ፤የክልል ፌዴሬሽኖች ፣ክለቦች፣ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እና ሌሎች ትልቅ ድርሻ ነበራቸው።
ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች የወከሉ እና የአገርን ሰንደቅ ከፍ ያደረጉ ብርቅዬ አትሌቶቻችን በውድድር ስፍራ በመገኘት አትሌቶችን በማበረታታት ምሳሌ በመሆን ያበረከታችሁት አስተዋፅኦ የሚደነቅ ነበር።
የፀጥታ አካላት የፌዴራል ፖሊሲ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ በቅንጅት በመሆን ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ ፌዴሬሽኑ በራሱ እና በአትሌቲክስ ወዳዱ የአገራችን ሕዝብ ስም ምስጋናን ያቀርባል።
ከፌዴሬሽናችን ጋር በአጋርነት እየሰሩ የሚገኙት አዲዳስ ፤ ኢትዮ ቴሌኮም ፣ ኮካኮላ ፣ኦሮሚያ ባንክ፣ ኤክሴል ትሬዲንግ ፣ጆርካ ኢቨንት፣የህክምና ባለሙያዎች ፣ቀይ መስቀል ማህበር ፣ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ውድድሩ በሰመረ መልኩ እንዲጠናቀቅ አብራችሁ ስለሰራችሁ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ።
ውድድሩ በቀጥታ ሽፋን እንዲያገኝ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፤ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለሕዝብ መረጃ ያደረሳቹ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች ለውድድሩ መሳካት ሚናቹ የጎላ ነበር ።
በጃን ሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በመገኘት የአገር ሀብት የሆኑ አትሌቶቻችንን ስታበረታቱ እና ስደግፉ የነበራቱ የማህበረሰብ ክፍሎች ላሳያችሁት ድጋፍ ፌድሬሽኑ ያመሰግናችኃል።
በ43ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር የታየው ተቀናጅቶ የመስራት ለቀጣይ ውድድሮች ምሳሌ የሚሆኑ እና አብሮ የመስራት ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ ነው።