የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እሁድ መስከረም 23 ቀን 2008 ዓ. ም. የ1 ቀን የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አለባቸው ንጉሴን ጨምሮ 7 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የተካሄደው የ2007 በጀት አመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በስልጠና፣ በውድድር፣ በማህበራት ማደራጃ፣ በማዘውተሪያ ስፍራዎችና በአጠቃላይ በአስተዳደራዊና የፋይናንስ እቅድ ክንውኖችና አፈፃፀሞች ላይ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ በቀጣይ አዲሱ በጀት አመት ትኩረት የሚሹ ጉዳዩችን በመለየት በተለይም በለውጥ ሂደት አተገባበር ላይ የጋራ መግባባት በመያዝ የግምገማው መድረክ ተጠናቋል፡፡


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting