5ኛው የሀገር አቀፍ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ኘሮግራም ምዘና ውድድር አጠቃላይ መረጃ 

          የውድድሩ ቀን፡-                                    ከነሐሴ 16-21/2009 ዓ.ም.

         የውድድሩ ቦታ፡-                                    ሀዋሳ

         የውድድሩ ተሳታፊዎች፡-                           ክልልና ከተማ አስተዳደሮች

         አዘጋጅ፡-                                              የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

         የፌዴሬሽኑ ኘሬዚዳንት፡-                          አትሌት ሻ/ቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ

         የፌዴሬሽኑ ም/ኘሬዚዳንት፡-                      አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም

         የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ፡-                        አቶ ቢልልኝ መቆያ

         የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ዳይሬክተር፡-                   የተከበሩ አቶ ዱቤ ጅሎ

         የተሳ/ውድ/ንዑ/የሥ/ሂደ/መሪ                       አቶ አስፋው ዳኜ

ጥቅል ኘሮግራም

        ነሀሴ 15/2009 ዓ.ም.  የቴክኒክ ስብሰባ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሀዋሳ ስታድየም

        ነሀሴ 16/2009 ዓ.ም. የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት

        ከነሀሴ 16-21/2009 ዓ.ም. ውድድሩ የሚካሄድባቸው ቀናት፡፡ 

5ኛው የሀገር አቀፍ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ኘሮግራም ምዘና ውድድር

ሕግና ደንብ

ዓላማ፡ -

 1. በክልሎችና በከተማ መስተዳድሮች የስልጠና ኘሮግራም ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤
 2. ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤
 3. የታዳጊዎች አትሌቲክስ ስልጠና ኘሮግራም አፈፃፀም ለመመዘን፤
 4. የላቀ ችሎታ ያላቸውን ተተኪ አትሌቶችን ለስፖርት አካዳሚ፣ ለአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት፣ ለክለቦችና ለብሔራዊ ቡድን ግብዓት እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር፤

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድሩ ደንብ

 1. የውድድሩ መጠሪያ፡-  ይህ ውድድር 5ኛው የሀገር አቀፍ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ኘሮግራም ምዘና ውድድር ተብሎ ይጠራል፡፡
  1. ውድድሩ የሚመራው፡- በፌዴራል ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ውድድር ህግና ደንብ መሠረት ይመራል፡፡
  2. ውድድሩን በበላይነት የሚመራ አካል፡- በፌዴራል ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ናቸው፡፡
 2. የውድድሩ አግባብነት፡- በአንድ የውድድር ተግባር ሦስት ቡድኖች ሦስትና ከሦስት በላይ አትሌቶች ተመዝግበው ለውድድር ከቀረቡ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በታች ከሆነ ግን ውድድሩ አይካሄድም፤
 3. የተወዳዳሪ ተገቢነት፡- በ5ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ፕሮግራም ምዘና ውድድር አውራ ደንብ አንቀጽ አራት መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
 4. በየክልሎችና  ከተማ አስተዳደሮች በት/ቤቶች እና ከት/ቤቶች ውጭ ተከፍተው ስልጠና እየወሰዱ ያሉ፣  የምዝገባ ሥርዓት አሟልተው የተገኙና የዕድሜ ገደባቸው በህክምና ኮሚቴ ታይቶ የተረጋገጠ እንዲሁም  በፌዴራል  ወጣቶችና ስፖርት ሚ/ር ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት መረጃ ቋት ውስጥ የተመዘገቡ ሰልጣኞች መሆን አለባቸው ለዚህም ማረጋገጫ በወቅቱ የተዘጋጀ ቴሴራ ሊያቀርቡ የሚችሉ ናቸው፤
 5. ተወዳዳሪዎች በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተከፈቱ ኘሮጀክት ጣቢያዎች የአትሌቲክስ ስልጠና ሲሰጥባቸው በቆዩበት የአትሌቲክስ ስልጠና ኘሮግራም ውስጥ የገቡ ስለመሆናቸው አስቀድሞ ስማቸው በፌዴራል ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ትምህርትና ስልጠና የስራ ሂደት ተመዘግበው በመረጃ ቋት ውስጥ ያሉና የተሟላ መረጃ ያላቸው ሰልጣኞች ብቻ ናቸው፡፡
 6.  በውድድሩ የሚሳተፉ አትሌቶች በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በማህተም የተረጋገጠና የስም ዝርዝራቸው የተላከ አትሌቶች ብቻ ናቸው፡፡
 7. በዚህ ውድድር የሚሳተፉ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስልጠና በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ሠልጣኞች የዕድሜ ገደባቸው በህክምና ኮሚቴ ታይቶ የተረጋገጠ መረጃ/ቅጽ/ ተሞልቶ አስቀድሞ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ለስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት በማቅረብ ተቀባይነት ያገኘ እና በምዝገባ መረጃ ቋት ውስጥ ስሙ ፣ ፎቶና ሌሎች አስፈላጊ የኘሮፋይል መረጃ ተሟልተው የገቡ ሠልጣኞች ሲሆኑ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ባጅ ይዘዉ መቅረብ ይኖርባቸዋል፤
 8. የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ የጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከል ማይጨው፣ ደብረብርሃን፣ በቆጂ እና ሀገረ ሠላም ማሠልጠኛ ማዕከል ውስጥ የሰለጠኑና በመሠልጠን ላይ ያሉ ሠልጣኞች በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችሉም፤

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

5ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ስልጠና ኘሮራግም ምዘና ውድድር ከነሐሴ 16-21/2009 ዓ.ም. በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል፡፡

አንቀጽ ሦስት

የውድድሩ አይነቶች

በ5ኛው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሥልጠና ኘሮግራም ምዘና ውድድሮች ከዚህ በታች እንደተገለፀው ይሆናል፡፡

ወንዶች ሴቶች
100 ሜትር 100 ሜትር
200 ሜትር 200 ሜትር
400 ሜትር 400 ሜትር
800 ሜትር 800 ሜትር
1500 ሜትር 1500 ሜትር
3000 ሜትር ቀጥታ 3000 ሜትር ቀጥታ
2000 ሜትር መሠናክል 2000 ሜትር መሠናክል
ርዝመት ዝላይ ርዝመት ዝላይ
ከፍታ ዝላይ ከፍታ ዝላይ
ሱሉስ ዝላይ ሱሉስ ዝላይ
ጦር ውርወራ (700 ግራም) ጦር ውርወራ (500 ግራም)
ዲስከስ ውርወራ (1.5 ኪ.ግ.) ዲስከስ ውርወራ (1 ኪ.ግ.)
አሎሎ ውርወራ (5 ኪ.ግ.) አሎሎ ውርወራ (3 ኪ.ግ.)
ድብልቅ ሪሌ
110 ሜትር መሠናክል 100 ሜትር መሠናክል
400 ሜትር መሠናክል 400 ሜትር መሠናክል
10000ሜ እርምጃ 5000ሜ እርምጃ

 

አንቀጽ አራት

የአትሌቶች ዕድሜ

 1. በዚህ ውድድር የሚሳተፋ አትሌቶች ዕድሜያቸው U-17 ማለትም ከ15-16 ዓመት ከ11 ወር ከ29 ቀን  የሆኑ ማለትም ከ1993-1994 ዓ.ም. የተወለዱ መሆን አለበት፤

አንቀጽ አምስት

በውድድር መሳተፍ 

          አንድ አትሌት በሁለት የግል እና ድብልቅ ሪሌ መወዳደር ይችላል፤ ነገር ግን ሁለቱም የሩጫ ተግባራት ከሆኑ አንደኛው የሩጫ ተግባር ከ200 ሜትር በላይ መሆን አለበት፡፡

አንቀጽ ስድስት

ምዝገባ

 1. በ2009 ዓ.ም. በሚካሄደው አገር አቀፍ ታዳጊዎች አትሌቲከስ ሻምፒዮና ውድድር የተሳታፊዎች ምዝገባ የሚካሄደው  እስከ ነሐሴ 1-8/2009 ዓ.ም. ለፌዴራል ወ/ስ/ሚኒስቴር ለምዘገባ የተላከውን የምዝገባ ኮፒ ለብሔራዊ ፌዴሬሽን በመላክ ጭምር ይሆናል፡፡
 2. ማንኛውም ተሳታፊ ቡድን በየውድድር ተግባሩ ከነተጠባባቂው አራት አትሌቶች ማስመዝገብ ይችላል፡፡
 3. የተወዳዳሪዎች ዝርዝር የሚላከው ከዚህ ውድድር ደንብ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ መሠረት ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሰባት

የድብልቅ ሪሌ (Mixed Relays)

 1. ድብልቅ ሪሌ (Mixed relay) ሁለት ወንድና ሁለት ሴት አትሌቶች እያንዳንዳቸው 400 ሜትር ወንድ ፣ ሴት፣ ወንድ ፣ ሴት አሰላለፍ መሠረት በመፈራረቅ የሚሮጥ ሩጫ ነው፡፡

አንቀጽ ስምንት

የተወዳዳሪ ቅያሪ

 1. ማንኛውም ቡድን በየውድድር ተግባሩ በየቀኑ የተወዳዳሪ ለውጥ ማድረግ ከፈለገ በየውድድሩ ዋዜማ (eve of each event) እስከ ቀኑ 3፡00 ሰዓት /ለኢቨንቱ/ ከተመዘገቡት አራት አትሌቶች ውስጥ ለቅያሪ በተዘጋጀው መቀየሪያ ቅጽ አትሌቶችን በማስመዝገብ የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ለሚቀርበው የተወዳዳሪዎች ቅያሪ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 2. ለድብልቅ ሪሌ የተወዳዳሪዎች ጥንቅርና የአሯሯጥ ቅደም ተከተል ምዝገባ የሚካሄደው ቀደም ሲል ለዱላ ቅብብል ከተመዘገቡት አትሌቶች ውስጥ  ውድድር ከመጀመሩ ከአንድ ሰዓት በፊት ለቴክኒካል መረጃ ክፍል ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡
  1. ለዱላ ቅብብል ከተመዘገቡት ከማንኛውም የውድድር ተግባራት ቀይሮ ማወዳደር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያው ዙር ውድድር በኋላ መቀየር የሚቻለው ሁለት አትሌቶችን ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

የአትሌቱ ጤንነት

በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተሟላ አትሌት በውድድሩ ተሳትፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው እራሱ ክልሉ፣ ከተማ አስተዳድሩ፣ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡

 

አንቀጽ አስር

ውጤትን ስለመግለጽ

 1. የዕለቱ ውድድር ውጤቶች ለተወዳዳሪዎችና ለቡድኖች በየውድድሩ ጣልቃ በአስተዋዋቂና በኮሙኒኬ ይገለፃል፡፡
 2. በተገለጹት ውጤቶች ላይ ስህተቶች ካሉ ወዲያውኑ የቡድን መሪው/አሠልጣኝ የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) በመቅረብ የማስተካከያ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡
 3. ከውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) የውድድሩ ውጤት ይፋ ሳይደረግ ውጤቱን መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሁኔታን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፋ በሆነ በ30 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው ለውድድሩ ዋና ዳኛ (refree) በቃል በአትሌቱ፣ አትሌቱን በሚወክለው ወይም በቡድን መሪው አማካይነት ሊሆን ይችላል፡፡ የውድድሩ ዋና ዳኛ ውሳኔ ሊሰጥ ወይም ጉዳዩን ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ያቀርባል፡፡ በፌዴሬሽኑ ክስ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ያልተስማማ ቡድን በፌዴራል ደረጃ ለተቋቋመው የውድድርና ሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ 1,500.00(አንድ ሺ አምስት መቶ ብር) በማስያዝ ቅሬታውን ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የቀረበው ቅሬታ ትክክል ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ይሆናል፡፡

 

አንቀጽ አስራ ሁለት

አለባበስ

ማንኛውም ተወዳዳሪ የክልሉን ወይም የከተማ መስተዳደሩን መለያ የሆነውን የስፖርት ትጥቅ ለብሶ ለውድደርና ለሽልማት መቅረብ አለበት፤ መለያ ለብሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደርም ሆነ ሽልማት መቀበል አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፣ ቁጥሩ የሚለጠፈው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ የከፍታ ዝላይ ተወዳዳሪዎች አንድ የመወዳደሪያ ቁጥር ብቻ በደረት ወይም ከጀርባ ላይ ለጥፎ መወዳደር ይችላሉ፡፡ በድብልቅ ሪሌ ውድድር አትሌቱ የክልሉን ወይም ከተማ አስተዳደሩን የሚገልጽ ጽሑፍ በደረቱ ላይ መለጠፍ አለበት፡፡ የመወዳደደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

በስም ጥሪ ቦታ በሰዓት መገኘት

ማንኛውም ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ45 ደቂቃ በፊት በስም ጥሪ ቦታ በመገኘት ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይኖርበታል፤ በስም ጥሪ ቦታ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የተወዳዳሪ ቴሴራ ወይም መታወቂያ

 1. ተወዳዳሪ አትሌቶች በክልል/ከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ወይም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህተም የተረጋገጠ ቴሴራ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ ቴሴራው አትሌቱ የታዳጊ ስልጠና ኘሮግራም ተሳታፊ መሆኑን የሚያሳይ ኘሮፋይል ወይም መረጃ አሟልቶ የያዘ መሆነ አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው ቴሴራ ወይም መታወቂያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ቴሴራ ወይም መታወቂያ የሌለው በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም፤
 2. በቴሴራው/መታወቂያው/ ላይ የትውልድ ዘመን መገለጽ አለበት

አንቀጽ አስራ ስድስት

ሽልማት

 1. በእያንዳንዱ የውድድር ተግባር ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁለቱም ፆታ የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፤
 2. በድብልቅ ሪሌ በእያንዳንዱ ጾታ 1ኛ ለሚወጣ ቡድን 4 ወርቅ፣ 2ኛ ለሚወጣ 4 ብር እና 3ኛ ለሚወጣ ቡድን 4 ነሐስ የሚሰጥ ሲሆን የነጥብ አሰጣጡ ግን አንደኛ ለሚወጣ 1 ወርቅ፣ 2ኛ ለሚወጣ አንድ ብር እና 3ኛ ለሚወጣ 1 ነሐስ ብቻ ይሆናል፡፡
 3. የዋንጫ ሽልማት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ5ኛው የሀገር አቀፍ ታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ኘሮግራም ምዘና አውራ ደንብ አንቀጽ ሃያ በተራ ቁጥር "ለ" በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት

ያልተገባ ፀባይ

ማንኛውም ተወዳዳሪ፣ አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ወጌሻ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ውድድሩ በሚከናወንበት ወቅት ያልተገባ ፀባይ ካሣየና ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ወይም የውድድር አዘጋጆች ሪፖርት ቀርቦ ጥፋቱ ከተረጋገጠ በኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተዘጋጀው የአሠልጣኞች፣ አትሌቶችና የክለቦች የሥነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ አስር መሠረት ይቀጣል፡፡ 

አንቀጽ አስራ ስምንት

በውድድሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት

 1. በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑ ቡድኖች የቡድናቸውን አርማ ይዘው በተሟላ ስፖርታዊ አለባበስ እንዲሁም ባህላዊ አልባሳትን ለብሰው በውድድሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት አለባቸው፤
 2. እንደአስፈላጊነቱ ከውድድር በኋላ በሚደረጉ ቴክኒካል ስብሰባዎች የቡድን መሪዎች/አሠልጣኞች መገኘት አለባቸው፡፡

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ

የቴክኒካል ስብሰባ

የቴክኒክ ስብሰባ ነሐሴ 15/2ዐዐ9 ዓ.ም ከቀኑ 4፡ዐዐ ሰዓት  በሀዋሳ ስታድየም ይካሄዳል፡፡ በስብሰባው ከየቡድኑ አንድ ቡድን መሪና አንድ አሠልጣኝ ብቻ ይሳተፋሉ፡፡

2009 ዓ.ም. አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ኘሮግራም ምዘና አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተወዳዳሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ __________________________________        ቀን _______________________

 

ተ.ቁ. ወንዶች የውድድሩ ዓይነት ሴቶች
1. 1. 100 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
2. 1. 200 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
3. 1. 400 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
4. 1. 800 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
5. 1. 1500 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
6. 1. 3000 ሜ. ቀጥታ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
7. 1. 2000 ሜ. መሠናክል 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
8. 1. 100/110 ሜ. መሠናክል 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
9. 1. 400 ሜ. መሠናክል 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
10. 1. ከፍታ ዝላይ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
ተ.ቁ. ወንዶች የውድድሩ ዓይነት ሴቶች
11. 1. ርዝመት ዝላይ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
12. 1. ሱሉስ ዝላይ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
13. 1.

እርምጃ

10000 ሜ/5000ሜ

1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
14. 1. ጦር ውርወራ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
15. 1. ዲስከስ ውርወራ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
16. 1. አሎሎ ውርወራ 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
17. 1.

ድብልቅ ሪሌ

4X400ሜ

1.
2. 2.
3. 3.


በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ በታዳጊና ወጣቶች ስልጠና ኘሮግራም ምዘና አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፋ አትሌቶች ማጠቃለያ መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ _______________________________________

 

ተ.ቁ. ሴቶች

 

የትውልድ ዘመን

ተ.ቁ. ወንዶች

 

የትውልድ ዘመን

የአትሌቷ ስም የአትሌቱ ስም
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           
           


በ2009 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ በታዳጊና ወጣቶች ስልጠና ኘሮግራም ምዘና አትሌቲክስ ሻምፒዮና  የተሳታፊ ልዑካን ማጠቃለያ መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር _______________________________________

ተ.ቁ. ልዑካን ሴት ወንድ ድምር
1. ተወዳዳሪዎች      
2. ቡድን መሪዎች      
3. አሠልጣኞች      
4. ሀኪም      
5. ወጌሻ      
6. የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ      
  ድምር      

ቅጹን የሞላው

ስም _________________________________________

ቀን ___________________________________________

ፊርማ _________________________________

ኃላፊነት __________________________________________________

  

 

በ2009 ዓ.ም. የሀገር አቀፍ በታዳጊና ወጣቶች ስልጠና ኘሮጀክት ምዘና አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

1 ቀን ነሐሴ  16/2009 ዓ.ም.                           ማክሰኞ

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1 8፡00 ዲስከስ ውርወራ ሴት ፍፃሜ
2 8፡10 አሎሎ ወንድ  ፍፃሜ
3 8፡15 800 ሜትር ሴት ማጣሪያ
4 8፡35 800 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
5 8፡55 400 ሜትር ሴት ማጣሪያ
6 9፡15 400 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
7 9፡35 100 ሜትር ሴት ማጣሪያ
8 9፡55 100 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
9 10፡10 ዲስከስ ሴት ሽልማት
10 10፡15 አሎሎ ወንድ ሽልማት

  

2 ቀን ነሐሴ 17/2009 ዓ.ም.                            ረብዕ

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 3፡00 ርዝመት ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
2. 3፡05 ከፍታ ዝላይ ሴት ፍፃሜ
3. 3፡10 100 ሜትር መሠናክል ሴት ማጣሪያ
4. 3፡30 800 ሜትር ሴት ፍፃሜ
5. 3፡40 800 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
6. 3፡50 800 ሜትር ሴት ሽልማት
7. 4፡00 100 ሜትር ሴት ፍፃሜ
8. 4፡10 800 ሜትር ወንድ ሽልማት
9. 4፡25 100 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
10. 4፡35 100 ሜትር ሴት ሽልማት
11. 4:40  100 ሜትር ወንድ ሽልማት
12. 4፡45 ርዝመት ዝላይ ወንድ ሽልማት
13. 5፡00 ከፍታ ዝላይ ሴት ሽልማት

 

 

በ2009 ዓ.ም. የሀገር አቀፍ በታዳጊና ወጣቶች ስልጠና ኘሮጀክት ምዘና አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

3 ቀን ነሐሴ 18/2009 ዓ.ም.                            ሐሙስ

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 1፡30 5000 ሜ እርምጃ ሴት ፍፃሜ
2. 1፡40 10,000 እርምጃ ወንድ ፍፃሜ
3. 3፡30 ሱሉስ ዝላይ ሴት ፍፃሜ
4. 3፡40 ዲስከስ ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
5. 4፡00 2000 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
6. 4፡20 2000 ሜትር መሠናክል ሴት ሽልማት
7. 4፡25 400 ሜትር ሴት ፍፃሜ
8. 4፡35 400 ሜትር ሴት ሽልማት
9. 4፡40 400 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
10. 4፡50 400 ሜትር ወንድ ሽልማት
11. 5፡00 2000 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
12. 5፡20 ሱሉስ ዝላይ ሴት ሽልማት
13. 5፡25 ዲስከስ ወንድ ሽልማት
14. 5፡30 2000 ሜትር መሰናክል ወንድ ሽልማት

 

4 ቀን ነሐሴ 19/2009 ዓ.ም.        ዓርብ

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 3፡00 ጦር ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
2. 3፡05 አሎሎ ሴት ፍፃሜ
3. 3፡10 100 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
4. 3፡20 110 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
5. 3፡40 3000 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
6. 4፡00 ሱሉስ ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
7. 4፡00 100 ሜትር መሰ. ሴት ሽልማት
8. 4፡05 110 ሜትር መሰ. ወንድ ሽልማት
9. 4፡10 200 ሜትር ሴት ማጣሪያ
10. 4፡30 200 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
11. 4፡40 ጦር ውርወራ ወንድ ሽልማት
12. 4፡45 1500 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
13. 5፡05 ርዝመት ዝላይ ሴት ሽልማት
14. 5፡10 200 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
15. 5፡35 3000 ሜትር ወንድ ሽልማት
16. 5፡40 ሱሉስ ዝላይ ወንድ ሽልማት

 

 

በ2009 ዓ.ም. የሀገር አቀፍ በታዳጊና ወጣቶች ስልጠና ኘሮጀክት ምዘና አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

5 ቀን ነሐሴ 20/2009 ዓ.ም.               ቅዳሜ

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 3፡00 ከፍታ ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
2. 3፡05 ርዝመት ዝላይ ሴት ፍፃሜ
3. 4፡00 400 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
4. 4፡00 ጦር ውርወራ ሴት ፍፃሜ
5. 4፡20 400 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
6. 4፡40 400 ሜትር ሴት ሽልማት
7. 4፡45 400 ሜትር ወንድ ሽልማት
8. 4፡50 200 ሜትር ሴት ፍፃሜ
9. 5፡10 200 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
10. 5፡30 1500 ሜትር ሴት ፍፃሜ
11. 5፡35 200 ሜትር ሴት ሽልማት
12. 5፡40 1500 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
13. 5፡45 200 ሜትር ወንድ ሽልማት
14. 5፡50 1500 ሜትር ሴት ሽልማት
15. 5፡55 1500 ሜትር ወንድ ሽልማት
16. 6፡05 2000 ሜትር መሰ. ሴት ሽልማት
17. 6፡10 ከፍታ ዝላይ ወንድ ሽልማት
18. 6፡20 አሎሎ ሴት ሽልማት
19. 6፡25 ጦር ውርወራ ሴት ሽልማት

 

6 ቀን ነሐሴ 21/2009 ዓ.ም.               እሁድ

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 3፡30 3000 ሜትር ሴት ፍፃሜ
2. 3፡45 3000 ሜትር  ሽልማት ሴት ፍፃሜ
3. 3፡50 ድብልቅ ሪሌ ወንድ/ሴት ፍፃሜ
4. 4፡00 ድብልቅ ሪሌ ሽልማት ወንድ/ሴት ፍፃሜ

 

 

ማሳሰቢያ፡ - የውድድሩ ኘሮግራም እንደአስፈላጊነቱ ሊቀየር ወይም ሊሻሻል ይችላል፡፡

               የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting