የ16ኛው አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቡድኑ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት፤

በ16ኛው የኣለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ 2 ወርቅ፣ 3 ብር በድምሩ 5 ሜዳልያዎችና 11 ዲፕሎማዎችን በማግኘት ከ205 ተሳታፊ ሃገራት መካከል ከዓለም 7ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 3ኛ በመሆን ውድድሩን የፈፀመው የአትሌቲክስ ልኡካን ቡድናችን ዛሬ ነሃሴ 9/2009 ዓ. ም. ማለዳ 12፡35 ሰዓት ላይ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው የኢፌዲሪ ወ/ስ/ሚ/ር ሚኒስትር፣ ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት፣ ክቡር ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት፣ ልዩ ልዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር፣ የሄኒከን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች፣የልዩ ልዩ ስፖርት ክለባት አመራሮችና ጋዜጠኞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አቀባበል የተደረገለት ሲሆን የአበባ አሰጣጥ ሥነ ስርዓትም ተከናውኗል፡፡

ከአበባ አሰጣጡ በመቀጠልም የእንኳን ደስ አላችሁና ደህና መጣችሁ ንግግሮች በክቡር የኢአፌ ፕሬዝደንት፣ በክቡር የኢት/ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንትና በክቡር ሚ/ሩ በየተራ ተላልፏል፡፡

 

 

 

 

 

 

 


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting