አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2009 .ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ በአራራት ሆቴል 16ኛው የአለምአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያልዑካን ቡድንአባላት በታላቅ ድምቀት ተሸኝተዋል።

በፕሮግራሙ መሰረት ከቡድኑ አሰልጣኞች መካከል አሰልጣኝ ሻምበል ቶሎሳቆቱ፣ ከአትሌቶች መካከል ከወንዶች አትሌት አንዱአም ላክበልሁ እና ከሴቶች አትሌት አሰለፈች መርጋ ዝግጅታውንና ሽኝቱን አስመልክተው ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት አስተላልፈዋል፤ በተለይ የሆቴል ቆይታቸው፣ ስልጠናቸው፣ የቡድኑ የአንድነት መንፈስ፣ እንዲሁም በዝግጅቱ ወቅት ከፌዴሬሽኑ አመራሮች ሲደረግልላቸው ስለነበረው እገዛ ገልጸው ለተደረገላቸው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ እነሱም በበኩላቸው በውድድሩ ላይ የቻሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል

በሥነ ስርዓቱ ላይ የኢ...ወ/ስ/ሚ/ር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት / አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፣ የኢትዮጵያአትሌቲክስ ፌዴሬሽን /ፕሬዘዳንት አትሌት ገብረእግዚያብሄር ገብረማርያም፣እንዲሁምስመ ጥርናታላላቅ አትሌቶች አትሌት ስለሺ ስህንንና ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ፕሮግራሙን በንግግር የከፈተሲሆን የቡድን መንፈስ ከምንም ነገር በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወሳኝና አስፈላጊነቱን አስመልክቶ የሁሉንም አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና በአጠቃላይ በስፍራው የነበሩትን ተጋባዦች ቀልብየሳበምሳሌያዊ ንግግር አድርጓል።

ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ 12 የተለያዩ ቀለማትን የያዘ የከለር ማቅለሚያ እርሳሶችን በአንድነት ይዞ ከመሃል በተመረጠች አትሌት ሁሉንም በአንድነት እንድትሰብረው እድል የሰጣትሲሆን አትሌቷም 12ቱንም የማቅለሚያ እርሳሶች በአንድነት በመስበር ሙከራ አድርጋ እቅቷታል ምሳሌውንም በሚገባ ለታዳሚው ለማስረዳት ሁሉንም አንድ በአንድ እንድትሰብረው በድጋሚ ሰጥቷታል አትሌቷም ምንምሳትቸገር ማቅለሚያዎቹን አንድ አንድ ሰብራ ጥላቸዋለች።

ኃይሌ " አንድ ከሆናችሁ ማንም አያሸንፋችሁም ፤ ከተለያያችሁ እንኳን ጠንካራው ደካማው ያሸንፋችዋል፤ ስለዚህ እባካችሁ እንድ ሁኑ አትነጣጠሉ፤አንድነት ሃይልነው! ኢትዮጵያዊነትን አስቀድሙ፤ድል ከእናንተጋር ይሁን!!" በማለት መልዕክቱን አጠቃሏል።

ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ቀጥሎ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢ...ወ/ስ/ሚ/ርሚኒስትር ዲኤታ  አቶ ተስፋዬ ይገዙ ሲሆኑ የሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴን ሀሳብ በማጠናከር ሁሉም አትሌቶች በአንድነት ሆነው ከዚህ በፊት በትውልድ ቅብብሎሽ የመጣውን የኢትዮጵያዊያንን የአትሌቲክስ ጀግንነት እንዲደግሙ እና ከምንም በላይ ሃገራቸውን እንዲያስቀድሙ በአደራ መልክ አሳስበው በመልካም ምኞት መልዕክታቸው ንግግራቸውን አሳርገዋል።

በአራራትሆቴል የስራ ኃላፊዎች የተዘጋጀውን የኬክ መቁረስ መርሃግብር ተከትሎ የሰንደቅዓላማ ርክክብ  ተደርጎ መርሃግብሩ በእራት መስተንግዶ ላይ እያለ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለቡድኑ ጠቃሚ የሆነ የአንድነት መንፈስን የሚጭር መልእክት አስተላልፎ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting