እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!

 

10ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 131 የዓለም ሃገራት ተሳትፈውበት ዛሬ ሐምሌ 9/2009 ዓ. ም. ተጠናቋል፡፡

ኢትዮጵያም 4 የወርቅ፣ 3 የብርና 5 የነሃስ ሜዳልያ በድምሩ 12 ሜዳልያ በማግኘት አዘጋጇን ሃገር ኬንያን ተከትላ 5ኛ በመሆን ውድድሩን በድል አጠናቃለች፡፡

በዓለም ታዳጊዎች የአትሌቲክስ ታሪክ ይህ ውጤት በወርቅና በአጠቃላይ ሜዳልያ ብዛት ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበትከመሆኑም በላይ ባልተለመዱ ርቀቶች በጣም ጥሩ የሚባል ውጤት የታየበት ነው፡፡

25 ሃገራት በሜዳልያ ሰንረዥ የገቡ ሲሆን 15 ሃገራት ብቻ ወርቅ ተከፋፍለዋል፡፡

አትሌቶቻችን ሰኞ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ፡፡

 

 

የ10ኛውን የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዝርዝር የውጤት

 


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting