የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ42ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በ4 ወርቅ፣ በ4 ብር፣ በ1 ነሃስ፣ በድምሩ በ9 ሜዳልያዎች ከዓለምም ከአፍሪካም የ2ኝነት ደረጃን ይዞ ለተመለሰው የልኡካን ቡድኑ አባላት ከ420,000.00 ብር በላይ የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ለአትሌቶች፤

ወርቅ ላገኙ - ከ20,500.00 ብር በላይ፣
ብር ላገኙ - ከ13,100 ብር በላይ፣
ነሃስ ላገኙ - ከ9,300 ብር በላይ፣
ዲፕሎማ ላገኙ (ከ4ኛ - 8ኛ ለወጡ) - ከ5,600 ብር በላይ፣
ለተሳተፉ 2,500 ብር ለእያንዳንዳቸው፤

ለዋና አሰልጣኞች፤

ወርቅ ላስገኙ - ከ20,500.00 ብር በላይ፣
ብር ላስገኙ - ከ13,100 ብር በላይ፣
ነሃስ ላስገኙ - ከ9,300 ብር በላይ፣

ለም/ዋና አሰልጣኝ፤

ወርቅ ላስገኙ - ከ18,600 ብር በላይ፣

ለአሰልጣኝ፤

ወርቅ ላስገኙ - ከ13,100.00 ብር በላይ፣
ብር ላስገኙ - ከ9,300 ብር በላይ፣
ነሃስ ላስገኙ - ከ5,3600 ብር በላይ ፌዴሬሽኑ የሸለመ ሲሆን

የፌዴሬሽኑ ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም ባደረገው የሥነ ስርዓቱ መክፈቻ ንግግር የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቅሶ የቡድን መንፈሱን በተጀመረው አግባብ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባና የታዩ ጥቃቅን ክፍተቶች ከወዲሁ በሚደረግ ማስተካከያ እንደሚሻሻሉ ገልጧል፡፡

ከኢፌዲሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚ/ር ተወክለው የመጡት አቶ ተስፋዬ በቀለ የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር በተገኘው ውጤት የሚ/ር መ/ቤቱ ደስተኛ መሆኑንና በቀጣይ በሚኖሩ አህጉራዊና ዓለማቀፋዊ ውድድሮች ላይም መ/ቤቱ ከፌዴሬሽኑ ጋር አብሮ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting