የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር

አጠቃላይ መረጃ

                 የውድድሩ ቀን፡-                                     ሚያዝያ 14-15/2009 ዓ.ም.

         የውድድሩ ቦታ፡-                                    አዲስ አበቦ ስታድየም

         የውድድሩ ተሳታፊዎች፡-                             ክልል፣ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ማዕከላትና ተቋም

         አዘጋጅ፡-                                            የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

         የፌዴሬሽኑ ኘሬዚዳንት፡-                           አትሌት ሻ/ቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ

         የፌዴሬሽኑ ም/ኘሬዚዳንት፡-                        አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም

         የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ፡-                          አቶ ቢልልኝ መቆያ

         የአት/ስፖ/ማስ/ማል/አብ/ የስ/ ሂደ/ መሪና አስተባባሪ   የተከበሩ አቶ ዱቤ ጅሎ

         የተሳ/ውድ/ንዑ/የሥ/ሂደ/መሪ ተወካይ                  አቶ አስፋው ዳኜ

 

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር

ሕግና ደንብ

                                             

ዓላማ ፡ -

 1. እ.ኤ.አ ከጁን 29-ጁላይ 02/2017 በአልጄሪያ - ኡራን በሚደረገው 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው  የሚሳተፉ ወጣት አትሌቶችን ለመምረጥ ፤
 2. ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድሩ ደንብ

 1. የውድድሩ መጠሪያ፡-    ይህ ውድድር የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር ተብሎ ይጠራል፡፡
  1. ውድድሩ የሚመራው፡-   በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ውድድር ህግና ደንብ መሠረት    ይመራል፡፡
 2. ውድድሩን በበላይነት የሚመራ አካል፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
  1. የውድድሩ አግባብነት፡- ማንኛውም አትሌት መወዳደር የሚችለው ከጥር 5-9/2009 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ በተካሄደው 5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተወዳደረበት የውድድር ምድብ በዚህ ደንብ በአንቀጽ 5 በተገለፀው መሠረት  ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር ሚያዝያ 14-15/2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ  ስታድየም ይካሄዳል፡፡

አንቀጽ ሦስት

የውድድሩ አይነቶች

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር የሚደረጉ ውድድሮች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡

ወንዶች ሴቶች
100 ሜትር 100 ሜትር
200 ሜትር 200 ሜትር
400 ሜትር 400 ሜትር
800 ሜትር 800 ሜትር
1500 ሜትር 1500 ሜትር
10,000 ሜትር ርምጃ 10,000 ሜትር ርምጃ
5000 ሜትር 3000 ሜትር ቀጥታ
10,000 ሜትር 5000 ሜትር
ርዝመት ዝላይ ርዝመት ዝላይ
ከፍታ ዝላይ ከፍታ ዝላይ
ሱሉስ ዝላይ ሱሉስ ዝላይ
መዶሻ ጦር ውርወራ
ምርኩዝ ዝላይ ዲስከስ ውርወራ
ጦር ውርወራ አሎሎ ውርወራ
ዲስከስ ውርወራ 4 X 100 ሜትር
አሎሎ ውርወራ 4 X 400 ሜትር
4 X 100 ሜትር 100 ሜትር መሠናክል
4 X 400 ሜትር 400 ሜትር መሠናክል
110 ሜትር መሠናክል 3000 ሜትር መሠናክል
400 ሜትር መሠናክል
3000 ሜትር መሠናክል

አንቀጽ አራት

የአትሌቶች ዕድሜ

 1. በዚህ ውድድር ዕድሜያቸው 18 እና 19 ዓመት የሆኑ ማለትም /1990-1991 ዓ.ም./ ወይም እ.ኤ.አ ዲሴምበር 31, 1998-1999 የተወለዱ በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፤
 2. በዚህ  ውድድር ታዳጊዎች ማለትም 16 እና 17 ዓመት የሆኑ አትሌቶች /ከ1992-1993 ዓ.ም./ ወይም እ.ኤ.አ ዲሴምበር 2000-2001 የተወለዱ በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፤
 3. ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ከ1993 ዓ.ም. ወይም እ.ኤ.አ ዲሴምበር 31, 2001 በኋላ የተወለዱ በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችሉም፡፡
 4. ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት በላይ የሆኑ /በ1989 ወይም እ.ኤ.አ ዲሴምበር 31,1997 በፊት የተወለዱ/ በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችሉም፡፡
 5. ዕድሜያቸው 16 ወይም 17 የሆኑ አትሌቶች በሁለት የግል እና በአንድ ሪሌ ውድድር ብቻ ይሳተፋሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም የትራክ ኢቬንቶች ከሆኑ አንዱ ኢቬንት ከ200 ሜትር በላይ መሆን አለበት፡፡

አንቀጽ አምስት

የውድድሩ ተሳታፊዎች

በኢትዮጵያ ወጣቶች የማጣሪያ ውድድር ላይ የሚሳተፉ የክልል፣ ከተማ አስተዳደር፣ የተቋማት፣ የኢት/ወጣ/ስፖ/አካዳሚ፣ የጥሩነሽ ዲባባ አት/ማሰ/ማዕ ተወዳዳሪ አትሌቶች ባህር ዳር ከተማ ከጥር 5-9/2009 ዓ.ም. በተካሄደው 5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሻምፒዮና ላይ ተሳትፈው ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ደረጃና ውጤት ያላቸው አትሌቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በታች ከተዘረዘረው ውጪ ውጤት ያላቸው አትሌቶች መወዳደር አይፈቀድላቸውም፡፡

ወንዶች ደረጃ የውድድሩ ዓይነት ሴቶች ደረጃ
ከ1ኛ-6ኛ 100 ሜትር ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ 200 ሜትር ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ 400 ሜትር ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-8ኛ 800 ሜትር ከ1ኛ-8ኛ
ከ1ኛ-8ኛ 1500 ሜትር ከ1ኛ-8ኛ
ከ1ኛ-6ኛ 10,000 ሜትር ርምጃ ከ1ኛ-6ኛ
----- 3000 ሜ ከ1ኛ-12ኛ
ከ1ኛ-15ኛ 5000 ሜትር ከ1ኛ-15ኛ
ከ1ኛ-15ኛ 10,000 ሜትር -----
ከ1ኛ-6ኛ 4 X 100 ሜትር ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ 4 X 400 ሜትር ከ1ኛ-6ኛ
------ 100 ሜትር መሠናክል ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ 110 ሜትር መሠናክል -----
ከ1ኛ-6ኛ 400 ሜትር መሠናክል ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-12ኛ 3000 ሜትር መሠናክል ከ1ኛ-12ኛ
ከ1ኛ-6ኛ ርዝመት ዝላይ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ ሱሉስ ዝላይ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ ከፍታ ዝላይ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ ምርኩዝ ዝላይ ----
ከ1ኛ-6ኛ ጦር ውርወራ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ አሎሎ ውርወራ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ ዲስከስ ውርወራ ከ1ኛ-6ኛ
ከ1ኛ-6ኛ መዶሻ ውርወራ ----

 

አንቀጽ ስድስት

ምዝገባ

 1. ባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው 5ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ሻምፒዮና የተካፈሉና በአንቀጽ አምስት በተገለፀው የውድድር ዓይነትና ደረጃ ዝርዝር ውስጥ የተካተተ አትሌት መሠረት ምዝገባው ተካሂዷል፡፡

 

አንቀጽ ሰባት

የአትሌቱ ጤንነት

        በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተሟላ አትሌት ተሰልፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው እራሱ ክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ፣ ክለቡ፣ ተቋሙ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ስምንት

ውጤትን ስለመግለጽ

 1. የዕለቱ ውድድር ውጤቶች ለተወዳዳሪዎችና ለቡድኖች በየውድድሩ ጣልቃ በአስተዋዋቂ፣ በኮሙኒኬና በቻርት ይገለፃል፡፡
 2. በተገለጹት ውጤቶች ላይ ስህተቶች ካሉ ወዲያውኑ የቡድን መሪው/አሠልጣኝ የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) በመቅረብ የማስተካከያ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡
 3. ከውድድሩ ቴክኒካለ መረጃ ከፍል (TIC) የውድድሩን ውጤት ይፋ ሳይደረግ ውጤቱን ለሕዝብ መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ከ3ዐ ደቂቃ በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሁኔታን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፋ በሆነ በ30 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው በቃል በአትሌቱ፣ በአሠልጣኝ ወይም በቡድን መሪው አማካይነት የውድድር ዳኛው ውሳኔ መስጠት ወይም ጉዳዩን ለክስ ሰሚ ኮማቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡ ክሱም በ30 ደቂቃ ጊዜ ውሳኔ ያገኛል፡፡
 5. ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ሆኖ ክሱ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ብር ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል፡፡ ሆኖም በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ያልተስማማ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጹሑፍ አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል፡፡ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስር

አለባበስ

 1. ማንኛውም ተወዳዳሪ የክልሉን፣ የከተማ አስተዳደሩንና የክለቡን ማልያ የሆነውን የስፖርት ትጥቅ መልበስ አለበት፣ ማልያ ለብሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡
 2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ለሜዳሊያ ሽልማት ሲቀርብ የክልሉን፣ ከተማ አስተዳደሩን፣ የክለቡንና የተቋሙን መለያ ለብሶ መቅረብ አለበት፡፡ ማሊያ ለብሶ ያልቀረበ አትሌት አይሸለምም፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፤ ቁጥሩ የሚለጠፈው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ የምርኩዝ ዝላይና የከፍታ ዝላይ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ቁጥሩን ከፊት ወይም ከኋላ ለጥፎ መወዳደር ይችላሉ፡፡ የመወዳደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

በስም ጥሪ ቦታ በሰዓት መገኘት

          ማንኛውም ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ45 ደቂቃ በፊት በስም ጥሪ ቦታ በመገኘት ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡ በስም ጥሪ ቦታ ላይ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድደሩ ላይ መካፈል አይችልም፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

የተወዳዳሪ ቴሴራ ወይም መታወቂያ

 1. የክልል/ከተማ አስተዳድር ተወዳዳሪ አትሌቶች በስም ጥሪ ቦታ ማንነታቸውን የሚገልጽ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንዲሁም የክለብ ተወዳዳሪዎች የክለባቸውን ቴሴራ ይዘው መቅረብ አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ያለው ቴሴራ ወይም መታወቂያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ቴሴራ የሌለው አትሌት በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
 2. በቴሴራው ላይ የትውልድ ዘመን መገለጽ አለበት፤
 3. ፖስፖርት ያላቸው አትሌቶች ፖስፖርታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ፌዴሬሽኑ አትሌቶቹ በሚያቀርቡት ቴሴራ ላይ እምነት ከሌለው ለማወዳደር አይገደድም፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቡድን ኮታ

 1. አማራ ክልል 54 አትሌቶች 3 አሠልጣኞች 1 የቡድን መሪ በድምሩ 58 ሰው፤
 2. ኦሮሚያ ክልል 78  አትሌቶች 5 አሠልጣኞች 1 ቡድን መሪ  በድምሩ 84 ሰው፤
 3. ደቡብ ክልል 5 አትሌት 1 አሠልጣኝ በድምሩ 6 ሰው፤
 4. አዲስ አበባ አስተዳደር 4 አትሌቶች እና 1 አሠልጣኝ በድምሩ 5 ሰው፤
 5. መከላከያ ስፖርት ክለብ 30 አትሌቶች 2 አሠልጣኞች 1 የቡድን መሪ በድምሩ 33 ሰው፤
 6. ሲዳማ በና 41 አትሌቶች 3 አሠልጣኞች 1 የቡድን መሪ በድምሩ 45 ሰው፤
 7. ጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከል 29 አትሌቶች 2 አሠልጣኞች 1 ቡድን መሪ በድምሩ  32  ሰው፤
 8. ኢት/ኤሌትሪክ 18 አትሌቶች 2 አሠልጣኝ 1 የቡድን መሪ በድምሩ 21 ሰው፤
 9. ኢት/ንግድ ባንክ 18 አትሌቶች 2 አሠልጣኝ 1 ቡድን መሪ ድምሩ 21 ሰው፤
 10. ደቡብ ፖሊስ 7 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ ጨምሮ በድምሩ 8 ሰው፤
 11. የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ 10 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ 1 ቡድን መሪ በድምሩ 12 ሰው፤
 12. ፌዴራል ማረሚያ 6 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ  በድምሩ 7 ሰው ፤
 13. ፌዴራል ፖሊስ 3 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ በድምሩ 4 ሰው፤
 14. መስፍን ኢንጅነሪንግ 11 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ 1 የቡድን መሪ በድምሩ 12 ሰው፤
 15. ትራንስ ኢትዮጵያ 6 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ በድምሩ 7 ሰው፤
 16. ኦሮሚያ ፖሊስ 2 አትሌቶች በድምሩ 2 ሰው፤
 17. አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 2 አትሌቶች፤
 18. ሱር ኮንስትራክሽን 4 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ በድምሩ 5 ሰው፤
 1. ሃዋሳ ከነማ 7 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ በድምሩ 8 ሰው፤
 2. ትግራይ ክልል 9 አትሌቶች 1 አሠልጣኝ በድምሩ 10 ሰው፤
 3. ሙገር ሲሚንት 2 አትሌቶች በድምሩ 2 ሰው፤
 4. ኦሮሚያ ውሃ ስፖርት 1 አትሌት  ሲሆን፡፡ ከተሰጠው ኮታ ውጪ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ክለቦች እና ተቋማት ወጪያቸውን በመሸፈን ተጨማሪ ባለሙያዎችን ማሳተፍ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የሥነ-ሥርዓት ጉድለት

          ማንኛውም ተወዳዳሪ፣ አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ወጌሻ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ውድድሩ በሚከናወንበት ወቅት የሥነ-ሥርዓት ጉድለት ካሣየና/ች ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ወይም የውድድር አዘጋጆች ሪፖርት ቀርቦ ጥፋቱ ከተረጋገጠ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተዘጋጀው የአሠልጣኞች፣ አትሌቶችና የክለቦች የሥነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ አስር ንዑስ አንቀጽ መሠረት ይቀጣል፡፡

አንቀጽ  አስራ ስድስት

የዶፒንግ ምርመራ

          የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር የዓለም አቀፉ ፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ፀረ ዶፒንግ ኦርጋናይዜሽን ሕግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት ከውድድሩ በፊት እና ከውድድሩ በኋላ የዶፒንግ ምርመራ ይከናወናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሰባት

የቴክኒካል ስብሰባ

የቴክኒካል ስብሰባ ሚያዝያ 13/2009 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡ በስብሰባው ላይ ከክልል፣ ከተማ አስተዳደርና ተቋም አካዳሚ በተላከው ዝርዝር መሠረት፡ ከየቡድኑ አንድ የቡድን መሪና አንድ አሠልጣኝ ብቻ ይሳተፋሉ፡፡

የቴክኒካል ስብሰባ አጀንዳዎች

 1. የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር
 2. የውድድሩን አመራሮች፣ የክስ ሰሚ ኮሚቴ፣ ዋና ዳኞች /technical officials/ ማስተዋወቅ
 3. የክስ ሂደትን መግለጽ፤
 4. የውድድሩን ኘሮግራም ማስተዋወቅ፤
 5. የመምና የሜዳ ተግባራት ውድድር ሂደት መግለጽ፤
 6. የደረት ቁጥር አጠቃቀም መግለጽ፤
 7. የከፍታ ዝላይና የምርኩዝ ዝላይ መነሻ ከፍታዎችና ጭማሪያቸውን /Starting height and subsequent height/ መግለጽ
 8. ለተጠየቁት የጽሑፍ ጥያቄዎች መልስ መስጠት


የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶች
ማጠቃለያ መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ክለብ/ተቋም _______________________________________

ወንዶች   ሴቶች
ተ.ቁ. የአትሌቱ ስም የትውልድ ዘመን   ተ.ቁ. የአትሌቷ ስም

የትውልድ

ዘመን

             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             


የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር ልዑካን ቡድን ማጠቃለያ መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ክለብ _______________________________________

ተ.ቁ. ልዑካን ሴት ወንድ ድምር
1. ተወዳዳሪዎች      
2. ቡድን መሪዎች      
3. አሠልጣኞች      
4. ሀኪም      
5. ወጌሻ      
6. የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ      
  ድምር      

ቅጹን የሞላው

ስም _________________________________________

ቀን ___________________________________________

ፊርማ _________________________________

ኃላፊነት ___________________________________________________

 

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር ኘሮግራም

1ኛ ቀን  ሚያዝያ 14/2009                         ጠዋት

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 1፡00 10,000 ሜትር እርምጃ ወንድ ፍፃሜ
2. 2፡00 አሎሎ ውርወራ ሴት ፍፃሜ
3. 2፡05 ስሉስ ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
4. 2፡10 ምርኩዝ ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
5. 2፡30 10,000 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
6. 3፡10 100 ሜትር ሴት ፍፃሜ
7. 3፡15 200 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
8. 3፡25 አሎሎ ሴት ሽልማት
9. 3፡30 400 ሜትር ሴት ፍፃሜ
10. 3፡40 10,000 ሜትር ወንድ ሽልማት
11. 3፡45 ስሉስ ዝላይ ወንድ ሽልማት
12. 3፡50 800 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
13. 3፡55 ዲስከስ ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
14. 4፡00 ርዝመት ዝላይ ሴት ፍፃሜ
15. 4፡00 ምርኩዝ ዝላይ ወንድ ሽልማት
16. 4፡05 100 ሜትር ሴት ሽልማት
17. 4፡10 200 ሜ ወንድ ሽልማት
18. 4፡15 3000 ሜትር መሠ. ወንድ ፍፃሜ
19. 4፡30 3000 ሜትር ሴት ፍፃሜ
20. 4፡45 400 ሜትር ሴት ሽልማት
21. 4፡55 800 ሜትር ወንድ ሽልማት
22. 5፡00 100 ሜትር መሠ. ሴት ፍፃሜ
23. 5፡10 110 ሜትር መሠ. ወንድ ፍፃሜ
24. 5፡20 ዲስከስ ውርወራ ወንድ ሽልማት
25. 5፡25 ርዝመት ዝላይ ሴት ሽልማት
26. 5፡30 1500 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
27. 5፡40 3000 ሜትር መሠ. ወንድ ሽልማት
28. 5፡45 3000 ሜትር ሴት ሽልማት
29. 5፡45 ጦር ውርወራ ሴት ፍፃሜ
30. 5፡45 ከፍታ ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
31. 5፡45 100 ሜትር መሠ. ሴት ሽልማት
32. 6፡00 110 ሜትር መሠ. ወንድ ሽልማት
33. 6፡05 4X100 ሜትር ሴት ፍፃሜ
34. 6፡15 4X400 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
35. 6፡25 1500 ሜትር ወንድ ሽልማት
36. 6፡30 4X100 ሜትር ሴት ሽልማት
37. 6፡35 4X400 ሜትር ወንድ ሽልማት

 

 

 

የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር ኘሮግራም

 

2ኛ ቀን  ሚያዝያ 15/2009                        ጠዋት

         

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 1፡00 10,000 ሜትር እርምጃ ሴት ፍፃሜ
2. 1፡00 መዶሻ ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
3. 2፡00 አሎሎ ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
4. 2፡05 ሱሉስ ዝላይ ሴት ፍፃሜ
5. 2፡05 5000 ሜትር ሴት ፍፃሜ
6. 2፡25 100 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
7. 2፡35 10,000 ሜትር እርምጃ ሴት ሽልማት
8. 2፡40 5000 ሜትር ሴት ሽልማት
9. 2፡45 200 ሜትር ሴት ፍፃሜ
10. 2፡55 400 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
11. 3፡05 አሎሎ ውርወራ ወንድ ሽልማት
12. 3፡10 ስሉስ ዝላይ ሴት ሽልማት
13. 3፡15 800 ሜትር ሴት ፍፃሜ
14. 3፡15 ዲስከስ ውርወራ ሴት ፍፃሜ
15. 3፡20 ርዝመት ዝላይ ወንድ ፍፃሜ
16. 3፡30 መዶሻ ውርወራ ወንድ ሽልማት
17. 3፡35 100 ሜትር ወንድ ሽልማት
18. 3፡40 200 ሜትር ሴት ሽልማት
19. 3፡45 3000 ሜ መሠ. ሴት ፍፃሜ
20. 4፡00 5000 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
21. 4፡20 400 ሜትር ወንድ ሽልማት
22. 4፡25 800 ሜትር ሴት ሽልማት
23. 4፡30 400 ሜትር መሠ. ሴት ፍፃሜ
24. 4፡40 400 ሜትር መሠ. ወንድ ፍፃሜ
25. 4፡50 ዲስከስ ውርወራ ሴት ሽልማት
26. 4፡55 ርዝመት ዝላይ ወንድ ሽልማት
27. 5፡00 1500 ሜትር ሴት ፍፃሜ
28. 5፡10 ጦር ውርወራ ወንድ ፍፃሜ
29. 5፡15 ከፍታ ዝላይ ሴት ፍፃሜ
30. 5፡15 3000 ሜትር መሠ. ሴት ሽልማት
31. 5፡20 5000 ሜትር ወንድ ሽልማት
32. 5፡25 400 ሜትር መሠ. ሴት ሽልማት
33. 5፡30 1500 ሜትር ሴት ሽልማት
34. 5፡35 4X100 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
35. 5፡45 4X400 ሜትር ሴት ፍፃሜ
36. 6፡05 4X100 ሜትር ወንድ ሽልማት
37. 6፡10 4X400 ሜትር ሴት ሽልማት
38. 6፡15 ጦር ውርወራ ወንድ ሽልማት
39. 6፡20 ከፍታ ዝላይ ሴት ሽልማት

ማ  ሳ  ሰ  ቢ  ያ

-       ይህ ኘሮግራም እንደ አስፈላጊነቱ  ሊሻሻል ወይም ሊቀየር ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Attachments:
Download this file (የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድር ደንብ.pdf)ሕግና ደንብ[ የኢትዮጵያ የወጣቶች አትሌቲክስ የማጣሪያ ውድድር]409 kB

Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting