1ኛው የኢትዮጵያ የመካከለኛና የመሠናክል አትሌቲክስ ሻምፒዮና

አጠቃላይ መረጃ

               የውድድሩ ቀን፡-                                                      ከመጋቢት 30- ሚያዝያ 1/2009 ዓ.ም.

         የውድድሩ ቦታ፡-                                                       አዲስ አበቦ ስታድየም

         የውድድሩ ተሳታፊዎች፡-                                               ክልል፣ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ማዕከላትና ተቋም

         አዘጋጅ፡-                                                                 የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

         የፌዴሬሽኑ ኘሬዚዳንት፡-                                             አትሌት ሻ/ቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ

         የፌዴሬሽኑ ም/ኘሬዚዳንት፡-                                 አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም

         የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ፡-                                   አቶ ቢልልኝ መቆያ

         የአት/ስፖ/ማስ/ማል/አብ/ የስ/ ሂደ/ መሪና አስተባባሪ           የተከበሩ አቶ ዱቤ ጅሎ

         የተሳ/ውድ/ንዑ/የሥ/ሂደ/መሪ ተወካይ                        አቶ አስፋው ዳኜ

 

1ኛው የኢትዮጵያ የመካከለኛና የመሠናክል

አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሕግና ደንብ

ዓላማ

Þ    ለመካከለኛ  እና ለመሠናክል ሩጫ የውድድር ምድብ አትሌቶች ትኩረት በመስጠት ለማበረታት፤

Þ    ለአትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤

Þ    በቀጣይ የ5000 እና የ10,000 ሜትር ተተኪ አትሌቶች ከማፍራት አንፃር  የላቀ አስተዋጽኦ ለማድረግ፤

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድር ደንብ

 1. የውድድሩ መጠሪያ፡- ይህ ውድድር 1ኛው የመካከለኛና የመሠናክል ሩጫ ውድድር ተብሎ ይጠራል፤
 2. ውድድሩን የሚመራው፡-ውድድሩ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ሕግና ደንብ ይመራል፤
 3. ውድድሩን በበላይነት የሚመራ አካል፡- ውድድሩን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው፡፡
 4. የውድድሩ አግባብነት፡- በአንድ የውድድር ተግባር ሁለት ቡድኖች ተመዝግበው ለውድድር ከቀረቡ ውድድ ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በታች ቁጥር ያለው ቡድን ከተመዘገበ ውድድሩ አይካሄድም፡፡

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

ውድድሩ የሚካሄደው መጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 1/2009  ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ዘወትር ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሦሰት

የውድድሩ ተሳታፊዎች

በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እውቅና የተሰጣቸው ክለቦች እንዲሁም የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ተቋማት ናቸው፡፡

አንቀጽ አራት

የውድድር ዓይነቶች

ሴቶች ተግባር ወንዶች
ü  800 ሜትር ü 
ü  1500 ሜትር ü 
ü  3000 ሜትር መሠናክል ü 

 

አንቀጽ አምስት

ምዝገባ

 1. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው መጋቢት 18-25/2009  ዓ.ም. ይሆናል፤
 2. በውድድር የምዝገባ ገደብ ውስጥ ያልተመዘገበ ክለብ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መጋቢት 26/2009 ዓ.ም. ብቻ መመዝገብ ይችላል፡፡
 3. ዝገባ የሚካሄደው ጉርድ ሾላ በገኘው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ይሆናል፤
 4. በብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በመሰልጠን ላይ ያ አትሌቶች በክልላቸው መይም በክለባቸው ባይመረጡም በብሔራዊ ቡድን ተመዝግቦ ሊወዳደሩ ይችላሉ፡፡
 5. ማንኛውም ምዝገባ የአትሌቶች የትውልድ ዘመን ማካተት አለበት፤

አንቀጽ ስድስት

ዕድሜ

 1. ማንኛውም አትሌት በውድድር ዓመቱ 16 ዓመት የሞላው /በ1993 ዓ.ም./ ወይም እ.ኤ.አ በ2001 የተወለደ ወይም ከዚያ በፊት የተወለደ በውድድሩ መሳተፍ ይችላል፡፡ ነገር ግን ዕድሜው ከ16 ዓመት በታች የሆነ አትሌት በዚህ ውድድር መሳተፍ አይችልም፡፡

አንቀጽ ሰባት

የአትሌቱ ጤንነት

 1. በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተጠበቀ አትሌት ተሰልፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው እራሱ ክልሉ/ከተማ አስተዳድሩ፣ ክለቡ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡ ፌዴሬሽኑ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

አንቀጽ ስምንት

ውጤት ስለመግለጽ

 1. የዕለቱ ውድድር ውጤቶች ለተወዳዳሪዎችና ለቡድኖች በየውድድሩ ጣልቃ በአስተዋዋቂ፣ በኮሙኒኬና በማስታወቂያ ሰሌዳ ይገለጻል፡፡
 2. በተገለጹት ውጤቶች ላይ ስህተቶች ካሉ ወዲያውኑ የቡድን መሪው /አሰልጣኙ የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) በመቅረብ የማስተካከያ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡
 3. ከውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) የውድድሩን ውጤት ይፋ ሳይደረግ ውጤቱን ለሕዝብ መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ  የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ30 ደቂቃ በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሁኔታን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፋ በሆነ በ3ዐ ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው በቃል በአትሌቱ፣ በአሰልጣኙ ወይም በቡድን መሪው አማካይነት ለውድድሩ ዳኛ ይሆናል፡፡ የውድድር ዳኛው ውሳኔ መስጠት ወይም ጉዳዩን ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ክስ ማቅረብ ይችላል፤ ክሱም በ30 ደቂቃ ጊዜ ውሳኔ ያገኛል፡፡ ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ይሆናል፡፡ ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ብር ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል፡፡ ውሳኔውም የመጨረሻ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስር

አለባበስ

ማንኛውም ተወዳዳሪ የክልሉን፣ ከተማ አስተዳደሩን፣ የክለቡንና የማሠልጠኛ ማዕከሉን መለያ የሆነው የስፖርት ትጥቅ መልበስ አለበት፤ መለያ ለብሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም፤ ከዚህም በተጨማሪ የቡድኑን መለያ ያልለበሰ ለሽልማት አይቀርብም፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፤ ቁጥሩ የሚለጠፈው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ የመወዳደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

በስም ጥሪ ቦታ በሰዓት መገኘት

ማንኛውም ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ45 ደቂቃ  በፊት በስም ጥሪ ቦታ በመገኘት ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይኖርበታል፤ በስም ጥሪ ቦታ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

የተወዳዳሪ ቴሴራ (ፖስፓርት)

 1. አትሌቶች በስም ጥሪ ቦታ ማንነታቸውን የሚገልጽ በዘመኑ የታደሰ የክለባቸውን ቴሴራ ወይም ፖስፓርት ይዘው መቅረብ አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ያለው ቴሴራ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ቴሴራ የሌለው ወይም ፖስርት አትሌት በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
 2. በቴሴራው ላይ የትውልድ ዘመን መገለጽ አለበት፤
 3. ፖስፓርት ያላቸው አትሌቶች ፖስፓርታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

ሽልማት

 1. በእያንዳንዱ የውድድር /ሪሌ/ ተግባር በቡድን ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁለቱም ጾታ የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ዳጐስ ያለ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡ የሽልማት መጠን ወደፊት ይገለፃል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

በውድድሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት

 1. በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑ ቡድኖች የቡድናቸውን አርማ ይዘው በተሟላ ስፖርታዊ አለባበስ እንዲሁም ባህላዊ አለባሳትን ለብሰው በውድደሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
 2. እንደ አስፈላጊነቱ ከውድድር በኋላ በሚደረጉ ቴክኒካል ስብሰባዎች የቡድን መሪዎች / አሰልጣኞች/ መገኘት አለባቸው

አንቀጽ አስራ ሥድስት

የቴክኒክ ስብሰባ

የቴክኒካል ስብሰባ መጋቢት 29/2009  ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
የ1ኛው ኢትዮጵያ የመካከለኛና መሠናክል ሩጫ ውድድር የተወዳዳሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ

1. ሴቶች 800 ሜትር ወንዶች
1. 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
2. 1. 1500 ሜትር 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.
3. 1. 3000 ሜትር መሠናክል 1.
2. 2.
3. 3.
4. 4.

ቅጹን የሞላው ሰው ስም________________________________________

ኃላፊነት____________________________________

ፊርማ_______________________________________

ቀን_________________________________________

የ1ኛው ኢትዮጵያ የመካከለኛና መሠናክል ሩጫ ውድድር የተወዳዳሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል/ከተማ አስተዳደር/ክለብ/ተቋም _______________________________________

ወንዶች   ሴቶች
ተ.ቁ. የአትሌቱ ስም የትውልድ ዘመን   ተ.ቁ. የአትሌቷ ስም የትውልድ ዘመን
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             
             

 

ቅጹን የሞላው ሰው ስም________________________________________

ኃላፊነት____________________________________

ፊርማ_______________________________________

ቀን_________________________________________

የ1ኛው ኢትዮጵያ የመካከለኛና መሠናክል ውድድር ኘሮግራም

1ኛ ቀን  መጋቢት 30/2009 ዓ.ም.                         ጠዋት

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 3፡00 1500 ሜትር ሴት ማጣሪያ
2. 3፡35 3000 ሜትር መሠናክል ወንድ ማጣሪያ
3. 4፡20 800 ሜትር ሴት ማጣሪያ
4. 4፡50 1500 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
5. 5፡25 3000 ሜትር መሠናክል ሴት ማጣሪያ
6. 6፡10 800 ሜትር ወንድ ማጣሪያ

 

 

 

 

2ኛ ቀን   ሚያዝያ 1/2009 ዓ.ም.                  ከሠዓት

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድሩ ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 8፡00 1500 ሜትር ሴት ፍፃሜ
2. 8፡10 3000 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
3. 8፡25 800 ሜትር ሴት ፍፃሜ
4. 8፡35 1500 ሜትር ሴት ሽልማት
5. 8፡40 3000 ሜትር መሠናክል ወንድ ሽልማት
6. 8፡45 1500 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
7. 8፡55 3000 ሜትር መሠ. ሴት ፍፃሜ
8. 9፡10 800 ሜትር ሴት ሽልማት
9. 9፡15 1500 ሜትር ሴት ሽልማት
10. 9፡20 800 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
11. 9፡30 3000 ሜትር መሠ. ሴት ሽልማት
12. 9፡35 800 ሜትር ወንድ ሽልማት

ማሳሰቢያ፡ - ይህ ኘሮግራም እንደአስፈላጊነቱ ሊሻሻል ወይም ሊቀር ይችላል፡፡

 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Attachments:
Download this file (1ኛው የኢትዮጵያ የመካከለኛ የመሰናክል ክልል ሩጫ ደንብ.pdf)ሕግና ደንብ[1ኛው የኢትዮጵያ የመካከለኛና የመሠናክል ሩጫ ዉድድር]670 kB

Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting