በ42ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሃገራችንን ወክሎ ኡጋንዳ ካምፓላ እሁድ መጋቢት 17/2009 ዓ. ም. የሚፋለመው ቡድናችን ሮብ መጋቢት 13/2009 ዓ.ም. ምሽት 12፡00 ሰዓት ላይ በአራራት ሆቴል ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡ በፌዴሬሽኑ አመራሮች የመልካም ምኞትና መመሪያም ተሰጥቷል፡፡
በኢአፌ ጽ/ቤት ኃላፊ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው ፕሮግራሙ በቡድኑ አሰልጣኞች፣ በአትሌቶች የስልጠና ዝግጅት ማብራሪያ፣ በኢአፌ ም/ፕሬዝደንት አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም የድልና መልክም ምኞት መግለጫና የውድድር መመሪያ፣ እንዲሁም በኢፌዲሪ ወ/ስ/ሚ/ር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ይገዙ አስተያየትና የመልክም ምኞት ንግግር የታጀበው አሸኛኘቱ ደማቅ ሆኖ አምሽቷል፡፡


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting