1ኛው የኢትዮጵያ ዱላ ቅብብል አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣

በአይነቱ ልዩ የሆነውና ለመጀመሪያ ጊዜ ከየካትቲ 24 - 25/2009 ዓ. ም. ለ2 ተከታታይ ቀናት በአዲስአበባ ስቴድዮም የኢትዮጵያ ዱላ ቅብብል አትሌቲክስ ሻምፒዮና ይካሄዳል፡፡

ለሃገራችን የአጭር ርቀት ተወዳዳሪ አትሌቶች ከፍተኛ የውድድር እድል ከመፍጠሩም በላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን ዝቅተኛ ሚኒማ የሚያሟሉ አትሌቶች ባሃማስ ላይ አፕሪል 22 – 23/2017 በሚካሄደው የመጀመሪያው የአለም ሪሌ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሃገራችንን የመወከል እድላቸው ሰፊ ይሆናል፡፡

በዚህ ውድድር ከ25 በላይ ቡድኖች /7 ክልልና 1 ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ/ ቁጥራቸው ወንዶች ከ267፣ ሴቶች ከ180 በድምሩ ከ447 በላይ ተሳታፊ አትሌቶች ይወዳደሩበታል፡፡

ማጣሪያዎቹን ጨምሮም ከ29 ያላነሱ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡

    የውድድር አይነቶቹ፣

  1. 4X100ሜ ሪሌ፣ በ2ቱም ፆታ ለየብቻ፣
  2. 4X200 ሜ ሪሌ፣ በ2ቱም ፆታ ለየብቻ፣
  3. 4X400 ሜ ሪሌ፣ በ2ቱም ፆታ ለየብቻ፣ 
  4. 4X800 ሜ. ሪሌ በ2ቱም ፆታ ለየብቻ ፣
  5. 4X400 ሜ ድብልቅ ሪሌ ሲሆኑ፡-

የቅብብል ሩጫ ውድድሮች በባህሪያቸው ማራኪና የተመልካችን ቀልብ የሚገዙ፣ ቁጭ ብድግ የሚያስብሉ በመሆናቸው ሁላችሁም ጠዋት ጠዋት አርብና ቅዳሜን በአዲስ አበባ ስቴድዮም ከእኛ ጋር ታሳልፉ ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting