የ2008 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ

ውድድር ካላንደር /ጊዜያዊ/

ተ.ቁ. ቀን የውድድር ዓይነት ከተማ
1. ታህሣሥ 14-17/2008 የአጭር፣የመካከለኛ፣ የሜዳ ተግባራትና ርምጃ ውድደር አዲስ አበባ
2. ጥር 22 /2008 33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር አዲስ አበባ
3. የካቲት 6/2008 9ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን /21 ኪ.ሜ./ ውድድር ሰበታ
4. የካቲት 20 /2008 17ኛው የሜ/ጄ/ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ 15 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ሐረሪ
5. መጋቢት 2007 5ኛው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ሃዋሳ
6. ከሚያዝያ 12-16/2008. 45ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዲስ አበባ
7. ከሚያዝያ 22-25/2008 የአለም አትሌቲክስ ቀን ውድድር አዲስ አበባ
8. ከግንቦት 10-12/2008 10ኛው የስፖርት ለሁሉም ፌስቲቫል አዲስ አበባ
9. ከግንቦት 25-28/2008 4ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሰላ
10. ሰኔ 19/2008 32ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሃዋሳ
11. ወደፊት ይገለፃል 4ኛው አገር አቀፍ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ስልጠና ኘሮጀክት ምዘና ውድድር ወደፊት ይገለፃል

 

የ2015/16 አህጉራዊና አለም አቀፍ ውድድሮች ካሌንደር

አህጉራዊ ውድድሮች (CAA)

 

ቀን የውድድር ዓይነት አገር/ከተማ

Sep. 3-19/2015

(ከነሐሴ 28/07-መስከረም 8/08)

10ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ብራዛቢል /ኮንጎ/
ወደፊት ይገለጻል 4ኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር ወደፊት ይገለጻል
ወደፊት ይገለጻል 20ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወደፊት ይገለጻል

የIAAF ውድድሮች

 

ቀን የውድድር ዓይነት አገር/ከተማ
Aug 22-30/2015 15ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቻይና /ቤጅንግ/
March 17-20/2016 የአለም የቤት ውስጥ ውድድር አሜሪካ /ፖርትላንድ/
March 26/2016 የአለም ግማሽ ማራቶን ውድድር እንግሊዝ /ካርድሊፍት/
July 19-24/2016 11ኛው የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ራሺያ /ካዛን/
Aug 05-21/2016 31ኛው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ብራዚል /ሬዮ ዲጄኔሮ/

 

የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት

አትሌቲክስ ውድድር ሕግና ደንብ

 

ዓላማ

      ለአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤

      በክለቦች መካከል የውድድር ዕድል ለመፍጠር፤

      ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድር ደንብ

 1. የውድድሩ መጠሪያ፡- ይህ ውድድር የኢትዮጵያ የክለቦች የአጭር፣ የመካከለኛ የሜዳ ተግባራትና የርምጃ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተብሎ ይጠራል፤
 2. ውድድሩን የሚመራው፡-ውድድሩ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ሕግና ደንብ ይመራል፤
 3. ውድድሩን በበላይነት የሚመራ አካል፡- ውድድሩን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው፡፡
 4. የውድድሩ አግባብነት፡- በአንድ የውድድር ተግባር ሁለት ቡድኖች እና ሶስትና ከሶስት በላይ አትሌቶች ተመዝግበው ለውድድር ከቀረቡ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በታች ቁጥር ያላቸው ቡድኖችና አትሌቶች ከተመዘገቡ ውድድሩ አይካሄድም፡፡ ነገር ግን ለውድድሩ ተመዝግበው ውድድሩን የሰረዘ ቡድን በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይቀጣል፡፡

 

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

ውድድሩ የሚካሄደው ከታህሣሥ 14-17/2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም ዘወትር ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ሦሰት

የውድድር ተሳታፊዎች

በዚህ ውድድር ላይ የሚሳተፋት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ክለቦች ሆነው በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እውቅና የተሰጣቸው ናቸው፡፡

 

አንቀጽ አራት

የውድድር ዓይነቶች

ሴቶች ተግባር ወንዶች
ü  100 ሜትር ü 
ü  200 ሜትር ü 
ü  400 ሜትር ü 
ü  800 ሜትር ü 
ü  1500 ሜትር ü 
ü  100 ሜትር መሰናክል -
- 110 ሜትር መሰናክል ü 
ü  400 ሜትር መሰናክል ü 
ü  3000 ሜትር መሰናክል ü 
ü  4 X 100 ሜትር ü 
ü  4 X 400 ሜትር ü 
ü  10,000 ሜትር ርምጃ/5000 እርምጃ ü 
ü  ርዝመት ዝላይ ü 
ü  ሱሉስ ዝላይ ü 
ü  ከፍታ ዝላይ ü 
- ምርኩዝ ዝላይ ü 
ü  አሎሎ ውርወራ ü 
ü  ዲስከስ ውርወራ ü 
ü  ጦር ውርወራ ü 
- መዶሻ ውርወራ ü 

አንቀጽ አምስት

ምዝገባ

 1. እያንዳንዱ ክለብ በየውድድር ተግባሩ እስከ አራት ተወዳዳሪዎች ማስመዝገብ ይላል፤
 2. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ከታህሣሥ 1-8/2008 ዓ.ም. ዓ.ም. ይሆናል፤
 3. በውድድር የምዝገባ ገደብ ውስጥ ያልተመዘገበ ክለብ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ታህሣሥ 11/2008 ዓ.ም. መመዝገብ አለበት፡፡
 4. ዝገባ የሚካሄደው ጉርድ ሾላ በገኘው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ይሆናል፤
 5. በብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በመሰልጠን ላይ ያ አትሌት ክለቡ ባይመርጠውም በግል ተመዝግቦ ሊወዳደር ይችላል፡፡ ነገር ግን ያገኘው ነጥብ ለክለቡ አይመዘገብም፤ በግሉ የሜዳሊያ ተሸላሚ ይሆናል፡፡

 

 

 

አንቀጽ ስድስት

ዕድሜ

 1. ታዳጊ፣ ወጣትና አዋቂ አትሌቶች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ታዳጊ ወንዶች በአሎሎና መዶሻ ውርወራ መሳተፍ አይችሉም፡፡ በዚሁ መሠረት በ2ዐዐ7 ዓ.ም. በ16 ዓመታቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገር በተደረጉ ውድድሮች የተሳተፋ አትሌቶች በዚህ ውድድር አይሳተፋም፤
 2. ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑት አትሌቶች /በ1992 ዓ.ም. እና ከዚያ በኋላ የተወለዱ/ በዚህ ወድድር መሳተፍ አይችሉም፡፡

 

አንቀጽ ሰባት

የተወዳዳሪ ቅያሪ

 1. ማንኛውም ቡድን በውድድር ተግባሩ የተወዳዳሪ ለውጥ ማድረግ ከፈለገ የቀጣይ ቀን ውድድር ከመደረጉ በፊት ዘወትር እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ለውድድሩ ከተመዘገቡት አትሌቶች ውስጥ ለቅያሪ በተዘጋጀው መቀየሪያ ቅጽ አትሌቶችን በመቀየር የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ለሚቀርበው የተወዳዳሪዎች ቅያሪ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 2. በዱላ ቅብብል የተወዳዳሪዎች ጥንቅርና የአሯሯጥ ቅደም ተከተል የሚደረገው የመጀመሪያው መድብ የዱላ ቅብብል ስም ጥሪ ከመደረጉ ከአንድ ሰዓት በፊት ለቴክኒካል መረጃ ክፍል ማሳወቅ አለባቸው፡፡
 3. ለዱላ ቅብብል ከተመዘገቡት ከማንኛውም የውድድር ተግባራት ቀይሮ ማወዳደር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያ ዙር በኋላ መቀየር የሚቻለው ሁለት አትሌቶችን ብቻ ነው፡፡

 

አንቀጽ ስምንት

የአትሌቱ ጤንነት

 1. በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተጠበቀ አትሌት ተሰልፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው እራሱ ክልሉ/ከተማ መስተዳድሩ፣ ክለቡ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡ ፌዴሬሽኑ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

 

አንቀጽ ዘጠኝ

ውጤት ስለመግለጽ

 1. የዕለቱ ውድድር ውጤቶች ለተወዳዳሪዎችና ለቡድኖች በየውድድሩ ጣልቃ በአስተዋዋቂ፣ በኮሙኒኬና በሠንጠረዥ ይገለጻል፡፡
 2. በተገለጹት ውጤቶች ላይ ስህተቶች ካሉ ወዲያውኑ የቡድን መሪው /አሰልጣኝ የውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) በመቅረብ የማስተካከያ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል፡፡
 3. ከውድድሩ ቴክኒካል መረጃ ክፍል (TIC) የውድድሩን ውጤት ይፋ ሳይደረግ ውጤቱን ለሕዝብ መግለጽ የተከለከለ ነው፡፡

አንቀጽ አስር

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሁኔታን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፊ በሆነ በ3ዐ ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው በቃል በአትሌቱ፣ በአሰልጣኙ ወይም በቡድን መሪው አማካይነት ሊሆን ይችላል፡፡ የውድድር ዳኛው ውሳኔ መስጠት ወይም ጉዳዩን ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ክስ ማቅረብ ይችላል ክሱም በ30 ደቂቃ ጊዜ ውሳኔ ያገኛል፡፡ ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ይሆናል፡፡ ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ብር ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ አንድ

አለባበስ

ማንኛውም ተወዳዳሪ የክለቡን መለያ የሆነው የስፖርት ትጥቅ መልበስ አለበት፤ መለያ ለበሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፤ ቁጥሩ የሚለጠፈው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ የምርኩዝ ዝላይና የከፍታ ዝላይ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ቁጥሩን በደረት ወይም ከጀርባ ላይ ለጥፎ መወዳደር ይችላሉ፡፡ የመወዳደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

በስም ጥሪ ቦታ በሰዓት መገኘት

ማንኛው ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ቢያንስ ከ45 ደቂቃ በፊት በስም ጥሪ ቦታ በመገኘት ውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይኖርበታል፤ በስም ጥሪ ቦታ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

 

 

አንቀጽ አስራ አራት

የተወዳዳሪ ቴሴራ ፖስፓርት

 1. አትሌቶች በስም ጥሪ ቦታ ማንነታቸውን የሚገልጽ በዘመኑ የታደሰ የክለብ ተወዳዳሪዎች የክለባቸውን ቴሴራ ይዘው መቅረብ አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ያለው ቴሴራ ወይም መታወቂያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ቴሴራ ወይም መታወቂያ የሌለው በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
 2. በቴሴራው ላይ የትውልድ ዘመን መገለጽ አለበት፤
 3. ፖስፓርት ያላቸው አትሌቶች ፖስፓርታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

ሽልማት

 1. በእያንዳንዱ የውድድር ተግባር ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁለቱም ጾታ የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 2. በውድድሩ በቡድን ነጥብ የወንድ አሸናፊ እና የሴት አሸናፊ ለየብቻቸው የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 3. የሴትና የወንድ ነጥብ /ውጤት/ ተደምሮ ለአጠቃላይ የቡድን አሸናፊ የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 4. በውድድሩ ሦስት ወርቅ እና ከዚያ በላይ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች ልዩ ሽልማት ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

በውድድሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት

 

 1. በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑ ቡድኖች የቡድናቸውን አርማ የዘው በተሟላ ስፖርታዊ አለባበስ እንዲሁም ባህላዊ አለባሳትን ለብሰው በውድደሩ መክፈቻና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
 2. እንደ አስፈላጊነቱ ከውድድር በኋላ በሚደረጉ ቴክኒካል ስብሰባዎች የቡድን መሪዎች / አሰልጣኞች መገኘት አለባቸው

 

አንቀጽ አስራ ሰባት

የቴክኒካል ስብሰባ

 

        የቴክኒካል ስብሰባ ታህሣሥ 13/2008 ዓ.ም. ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

 

 

የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት

አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

1ኛ ቀን       ሚያዝያ 6/2006 ዓ.ም.                             ሰኞ ጠዋት

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 2፡00 ርዝመት ዝላይ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
2. 2፡00 ዲስከስ ውርወራ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
3. 2፡00 100 ሜትር መሠናክል ሴት ግማሽ ፍፃሜ
4. 2፡25 110 ሜትር መሠናክል ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
5. 2፡50 800 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
6. 3፡20 800 ሜትር ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
7. 3፡50 400 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
8. 4፡20 100 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
9. 4፡50 100 ሜትር ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
10. 4፡50 ርዝመት ዝላይ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
11. 4፡50 ዲስከስ ውርወራ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
12. 4:50 ሽልማት /ርዝመት ዝላይ/ ሴት  
13. 5፡10 3000 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
14. 5፡30 3000 ሜትር መሠናክል ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
15. 5፡50 ሽልማት /ዲስከስ ውርወራ/ ወንድ  
16. 5፡55 ሽልማት /3000 ሜ. መሠናክል/ ሴት  
17. 6፡00 4 X 400 ሜትር ሴት ፍፃሜ
18. 6፡15 ሽልማት /ርዝመት ዝላይ/ ወንድ  
19. 6፡20 4 X 400 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
20. 6፡35 ሽልማት /ዲስከስ ውርወራ/ ሴት  
21. 6፡40 ሽልማት /4 X 400 ሜትር/ ሴት  
22. 6፡45 ሽልማት /4 X 400 ሜትር/ ወንድ  

 

የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት

አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

2ኛ ቀን      ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም.                              ማክሰኞ ጠዋት

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 2፡00 5000 ሜትር ርምጃ ሴት ፍፃሜ
2. 2፡30 10,000 ሜትር ርምጃ ወንድ ፍፃሜ
3. 2፡30 ከፍታ ዝላይ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
4. 2፡30 አሎሎ ውርወራ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
5. 3፡30 100 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
6. 3፡40 ሽልማት /5000 ሜ.ርምጃ/ ሴት  
7. 3፡45 110 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
8. 3፡55 ሽልማት /10,000 ሜ. ርምጃ/ ወንድ  
9. 4፡00 800 ሜትር ሴት ፍፃሜ
10. 4፡00 ጦር ውርወራ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
11. 4፡10 ሽልማት /100 ሜ.መሠ./ ሴት  
12. 4፡15 800 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
13. 4፡25 100 ሜትር ሴት ፍፃሜ
14. 4፡30 ሽልማት /110 ሜ. መሠናክል/ ወንድ  
15. 4፡35 100 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
16. 4፡40 ሽልማት /800 ሜትር/ ሴት  
17. 4፡45 400 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
18. 4፡55 ሽልማት /ከፍታ ዝላይ/ ሴት  
19. 5፡00 ሽልማት /አሎሎ ውርወራ/ ወንድ  
20. 5፡05 4 X 1500 ሜትር ሴት ፍፃሜ
21. 5፡25 ሽልማት /800 ሜ./ ሴት  
22. 5፡30 4 X 1500 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
23. 5፡50 ሽልማት /100 ሜ./ ሴት  
24. 5፡55 ሽልማት /100 ሜ./ ወንድ  
25. 6፡00 ሽልማት /400 ሜ./ ሴት  
26. 6፡05 ሽልማት /400 ሜ./ ወንድ  
27. 6፡10 ሽልማት /ጦር ውርወራ/ ወንድ  
28. 6፡15 ሽልማት /4 X 1500 ሜትር/ ሴት  
29. 6፡20 ሽልማት /4 X 1500 ሜትር/ ወንድ  

 

የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት

አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

3ኛ ቀን      ሚያዝያ 8/2006 ዓ.ም.                             ረቡዕ  ጠዋት

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 2፡00 ሱሉስ ዝላይ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
2. 2፡00 ከፍታ ዝላይ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
3. 2፡30 1500 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
4. 2፡50 1500 ሜትር ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
5. 3፡10 400 ሜትር መሠናክል ሴት ግማሽ ፍፃሜ
6. 3፡30 400 ሜትር መሠናክል ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
7. 3፡50 200 ሜትር ሴት ግማሽ ፍፃሜ
8. 4፡10 200 ሜትር ወንድ ማጣሪያ
9. 4፡10 አሎሎ ውርወራ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
10. 4፡10 ሱሉስ ዝላይ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
11. 4፡40 ሽልማት /ስሉስ ዝላይ/ ሴት  
12. 4፡45 ሽልማት /ከፍታ ዝላይ/ ወንድ  
13. 4፡50 200 ሜትር ወንድ ግማሽ ፍፃሜ
14. 5፡10 4 X 800 ሜትር ሴት ፍፃሜ
15. 5፡20 ሽልማት /አሎሎ ውርወራ/ ሴት  
16. 5፡25 4 X 800 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
17. 5፡50 ሽልማት /ስሉስ ዝላይ/ ወንድ  
18. 5፡55 ሽልማት /4 X 800 ሜትር/ ሴት  
19. 6፡00 ሽልማት /4 X 800 ሜትር/ ወንድ  

 

የኢትዮጵያ ክለቦች የአጭር፣ መካከለኛ፣ ርምጃና የሜዳ ተግባራት

አትሌቲክስ ውድድር ኘሮግራም

 

የተስተካከለ ኘሮግራም

 

4ኛ ቀን      ሚያዝያ 9/2006 ዓ.ም.                             ሐሙስ ጠዋት

 

ተ.ቁ. ሰዓት የውድድር ተግባር ፆታ የተግባሩ ዓይነት
1. 1፡00 መዶሻ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
2. 2፡30 ምርኩዝ ዝላይ ወንድ ማጣሪያና ፍፃሜ
3. 2፡30 ጦር ውርወራ ሴት ማጣሪያና ፍፃሜ
4. 2፡30 400 ሜትር መሠናክል ሴት ፍፃሜ
5. 2፡45 400 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
6. 3፡00 1500 ሜትር ሴት ፍፃሜ
7. 3፡10 ሽልማት /መዶሻ/ ወንድ  
8. 3፡15 1500 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
9. 3፡25 ሽልማት /ምርኩዝ ዝላይ/ ወንድ  
10. 3፡30 400 ሜትር ሴት ፍፃሜ
11. 3፡40 ሽልማት /ጦር ውርወራ/ ሴት  
12. 3፡45 400 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
13. 3፡55 ሽልማት /400 ሜ.መሠ./ ሴት  
14. 4፡00 200 ሜትር ሴት ፍፃሜ
15. 4፡10 ሽልማት /400 ሜ.መሠ./ ወንድ  
16. 4፡15 200 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
17. 4፡25 ሽልማት /1500 ሜ./ ሴት  
18. 4፡30 ሽልማት /1500 ሜ./ ወንድ  
19. 4፡35 3000 ሜትር መሠናክል ወንድ ፍፃሜ
20. 4፡55 ሽልማት /400 ሜ./ ሴት  
21. 5፡00 4 X 100 ሜትር ሴት ፍፃሜ
22. 5፡15 ሽልማት /400 ሜ./ ወንድ  
23. 5፡20 4 X 100 ሜትር ወንድ ፍፃሜ
24. 5፡35 ሽልማት /200 ሜትር/ ወንድ  
25. 5፡40 ሽልማት /3000 ሜ. መሠናክል/ ወንድ  
26. 5፡45 ሽልማት /200 ሜ./ ሴት  
27. 5፡50 ሽልማት /4 X 100 ሜትር/ ሴት  
28. 5፡55 ሽልማት /4 X 100 ሜትር/ ወንድ  

 

 

የ33ኛው ጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር

ሕግና ደንብ

                                             

ዓላማ፡- ክልሎችን፣ ከተማ አስተዳድሮችንና ክለቦችን በኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር በማሳተፍ የአትሌቶችን ወቅታዊ ብቃት በማወቅ እ.ኤ.አ. ማርች 22/2016 ካሜሮን በሚካሄደው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ውድድር የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ነው፡፡

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድሩ ደንብ

 1. 1.የውድድሩ መጠሪያ፡- ይህ ውድድር 33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ተብሎ ይጠራል፡፡
 2. 2.ውድድሩ የሚመራው፡- በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ህግና ደንብ መሠረት ይመራል፡፡
  1. 3.ውድድሩን በበላይነት የሚመራ አካል፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ቀን፣ ቦታና ሰዓት

የ33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ጥር 22/2ዐዐ8 ዓ.ም. በጃንሜዳ ከጠዋቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

አንቀጽ ሦስት

የውድድሩ አይነትና ርቀት /ካታጐሪ/

 

የውድድሩ ዓይነት ኢንተርናሽናል የጃንሜዳ ሀገር አቋራጭ ሲሆን ከዚህ በታች በተገለጸው ካታጐሪ መሠረት ይከናወናል፡-

 

በሴቶች

 • ”6” ኪ.ሜ ወጣት ሴቶች
 • ”8” ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች

በወንዶች

 • ”8” ኪ.ሜ ወጣት ወንዶች
 •  በ”12” ኪ.ሜ አዋቂ ወንዶች

አንቀጽ አራት

የአትሌቶች የዕድሜ ገደብ

 

 1. ማንኛውም ዕድሜው ከ18-19 ዓመት የሆነ ማለትም /ከ1989-1990 ዓ.ም./ (እ.ኤ.አ. 1996-1997) የተወለደ/ች አትሌት በወጣት ወይም በአዋቂ የውድድር ካታጐሪ መወዳደር ይችላል፡፡
 2. ማንኛውም ዕድሜው ከ16-17 ዓመት የሆነ ማለትም /ከ1991-1992 ዓ.ም./ (እ.ኤ.አ. ከ1999-2000) የተወለደ አትሌት በወጣት የውድድር ካታጐሪ ብቻ መሳተፍ ይችላል፡፡
 3. ማንኛውም ዕድሜው ከ19 ዓመት በላይ የሆነ አትሌት ማለትም /በ1989 ዓ.ም./ (እ.ኤ.አ. በ1997) የተወለደ በአዋቂዎች የውድድር ካታጐሪ ብቻ መሳተፍ አለበት፡፡
 4. ዕድሜው ከ16 ዓመት በታች የሆነ አትሌት ማለትም /ከ1992 ዓ.ም./ (እ.ኤ.አ. በ1999) በኋላ የተወለደ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡

 

አንቀጽ አምስት

ተሳታፊዎች

 

በ33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር የሚሳተፉ የክልል፣ የከተማ አስተዳድር፣ የክለብ፣ የማሠልጠኛ ተቋማት የግልና የሌሎች አገሮች ተወዳዳሪ አትሌቶች ናቸው፡፡

 

አንቀጽ ስድስት

ቡድኖች የሚያስመዘግቡት ተወዳዳሪዎች ብዛት

 1. ማንኛውም ክልል ከተማ አስተዳድርና ክለብ በ6 ኪ.ሜትር ወጣት ሴት፣ በ8 ኪ.ሜትር ወጣት ወንድ፣ በ8 ኪ.ሜትር አዋቂ ሴት እና በ12 ኪ.ሜትር አዋቂ ወንድ በእያንዳንዱ ካታጐሪ ከ4 - 12 አትሌቶችን ማስመዝገብ ይችላል፡፡

አንቀጽ ሰባት

የምዝገባ ጊዜ

 1. የ33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ከጥር 12-18/2ዐዐ8 ዓ.ም ድረስ ነው፡፡
 2. በውድድሩ የምዝገባ ጊዜ ገደብ ውስጥ ያልተመዘገበ ክልል፣ ከተማ መስተዳድርና ክለብ ብር 3ዐዐ (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጥር 19/2ዐዐ8 ዓ.ም ብቻ መመዝገብ አለበት፡፡
 3. የምዝገባ ቦታ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በተሰጡት የምዝገባ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡

አንቀጽ ስምንት

ስም ጥሪና መታወቂያ

 1. ተወዳዳሪ አትሌቶች በስም ጥሪ ቦታ ማንነታቸውን እና የክልል/የከተማ አስተዳደር ነዋሪ መሆናቸውን የሚገልጽ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንዲሁም የክለብ አትሌቶች የክለባቸውን ቴሴራ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
 2. የተወዳዳሪዎች ስም ጥሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ከ45 ደቂቃ በፊት ይከናወናል፡፡ የተወዳዳሪዎች ስም ጥሪ ከተከናወነ በኋላ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይቻልም፤ ተወዳድሮ የተገኘ አትሌት ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

የአትሌቶች ጤንነት

በውድድሩ ተካፋይ የሚሆን አትሌት ጤናው የተሟላ መሆን አለበት፤ ጤናው ያልተጠበቀ አትሌት ተሰልፎ ቢገኝና ጉዳት ቢደርስበት ተጠያቂ የሚሆነው ክልሉ/ከተማ መስተዳድሩ፣ ክለቡ እና አትሌቱ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስር

የሀገር ውክልና

በ33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ፌዴሬሽኑ ከክለቦች ይመርጣል፣ የተመረጡትም አትሌቶች ለክለቦቻቸው ጭምር ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡

 

አንቀጽ አስራ አንድ

የነጥብ አሰጣጥ

 1. በሁሉም የውድድር ካታጐሪ ከተመዘገቡት አስራ ሁለት አትሌቶች ውስጥ ቀድመው ውድድሩን ላጠናቀቁ አራት ተወዳዳሪዎች (Top 4) ነጥብ ይሰጣል፡፡ ከአራት አትሌቶች በታች ደረጃ ያስመዘገቡ ክልሎች፣ ከተማ መስተዳደሮች፣ ክለቦች እና አገሮች የቡድን ደረጃ ነጥብ ባይመዘገብላቸውም ባላቸው ውጤት መሠረት አትሌቶቹ በግል ይሸለማሉ፡፡
 2. ለእያንዳንዱ አትሌት በገባበት በግል ደረጃ መሠረት ውጤት ይመዘገባል፡፡ በቡድን ውጤት አሰጣጥ ከአነስተኛ ወደ ከፍተኛ ቁጥር የገባበት ደረጃ ተደምሮ አነስተኛ ነጥብ ያስመዘገበ ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡

ምሳሌ፡-

                  ቡድን ሀ = 1ኛ" 5ኛ" 8ኛና 12ኛ ቢወጡ - ድምር - 26 ይሆናል

ቡድን ለ= 2ኛ" 3ኛ" 6ኛና 1ዐኛ ቢወጡ - ድምር 21 ይሆናል

በዚህ ድምር ውጤት መሰረት አሸናፊ ቡድን ይሆናል ማለት ነው፡፡ የውጤት ድምራቸው እኩል ቢሆን መጨረሻ ነጥብ ያስመዘገበ /ዘጊው አትሌት/ ማለት ለአንደኛው የቀረበው አትሌት ቡድን አሸናፊ ይሆናል

ምሳሌ፡-

               ቡድን ሀ = 1ኛ" 5ኛ" 8ኛ፣ 9ኛ ቢወጡ - ድምራቸው - 23 ይሆናል

ቡድን ለ= 2ኛ" 3ኛ" 6ኛ፣ 12ኛ ቢወጡ - ድምራቸው 23 ይሆናል

ከላይ የተጠቀሱት 2 ቡድኖች ነጥባቸው እኩል ቢሆኑም ለአንደኛ የቀረበው የመጨረሻው /ዘጊው አትሌት/ 9ኛ የወጣ የ ቡድን ስለሆነ የቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

ክስና ይግባኝ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት ነው፡፡
 2. የውድድር ውጤቶችን ወይም የውድድር ተግባር ሂደትን በተመለከተ የክስ ጥያቄ የሚቀርበው ውጤቱ ይፋ በሆነ በ30 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
 3. ማንኛውም የክስ ጥያቄ መጀመሪያ የሚቀርበው በቃል በአትሌቱ፣ በአሠልጣኙ ወይም በቡድን መሪው አማካይነት ለውድድሩ ዳኛ (Cross Country referee) ይሆናል፡፡ የውድድር ዳኛው ውሳኔ መስጠት ወይም ጉዳዩን ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
 4. በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ አካል በጽሑፍ ከብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ ክስ ማቅረብ ይችላል፡፡ ክሱም በ30 ደቂቃ ጊዜ ውሳኔ ያገኛል፡፡
 5. ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ሆኖ ክሱ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ብር ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል፡፡

አንቀጽ አስራ ሦስት

አለባበስ

ማንኛውም ተወዳዳሪ የክልሉን፣ የከተማ መስተዳደሩን፣ የክለቡን/የተቋሙን የስፖርት ትጥቅ መልበስ አለበት፤ መለያ ለብሶ ያልቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ አስራ አራት

የመወዳደሪያ መሮጫ ቁጥር

ማንኛውም ተወዳዳሪ አትሌት የመወዳደሪያ ቁጥር ሊኖረው ይገባል፣ ቁጥሩ የሚለጠፈው ግልጽ ሆኖ በሚታይ ቦታ በደረትና በጀርባ ላይ ነው፡፡ የመወዳደደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቴክኒካል ስብሰባ ቀን ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

በውድድሩ ስፍራ በሰዓት መገኘት

ማንኛውም ተወዳዳሪ ውድድሩ ከመጀመሩ ከ45 ደቂቃ በፊት በውድድሩ ቦታ በመገኘት ለውድድሩ ዝግጁ መሆኑን ለስም ጠሪ ዳኞች ማሳወቅ ይኖርበታል፤ በስም ጥሪ ቦታ ተገኝቶ ስሙን ለስም ጠሪ ዳኞች ያላሳወቀ አትሌት በውድድሩ ላይ መካፈል አይችልም፤ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

የተወዳዳሪ መታወቂያ

የክልል/ከተማ መስተዳደር ተወዳዳሪ አትሌቶች በዳኞች ስም ጥሪ ቦታ ማንነታቸውን የሚገልጽ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንዲሁም የክለብ ተወዳዳሪዎች የክለባቸውን ቴሴራ ወይም ፓስፖርት ይዘው መቅረብ አለባቸው፤ ስርዝ ድልዝ ያለው መታወቂያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

 

አንቀጽ አስራ ሰባት

ሽልማት

 1. ከ1ኛ - 3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የወርቅ፣ የብር እና የነሐስ ሜዳልያ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 2. በውድድሩ ከ1ኛ - 6ኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁሉም የውድድር ካታጎሪዎች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 3. በአራቱም የውድድር ካታጐሪ በቡድን ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ ቡድኖች የሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፡፡
 4. የቡድን አሸናፊ ለሚሆኑ ለአራቱ ካታጐሪ ቡድኖች ለእያንዳንዳቸው የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ስምንት

የሥነ-ሥርዓት ጉድለት

ማንኛውም ተወዳዳሪ፣ አሰልጣኝ፣ የቡድን መሪ፣ ወጌሻ ወይም ሌሎች የቡድን አባላት ውድድሩ በሚከናወንበት ወቅት የሥነ-ሥርዓት ጉድለት ካሣየና ውድድሩን በሚመሩ ዳኞች ወይም የውድድር አዘጋጆች ሪፖርት ቀርቦ ጥፋቱ ከተረጋገጠ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተዘጋጀው የአሠልጣኞች፣ አትሌቶችና የክለቦች የሥነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ አስር መሠረት ይቀጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ

የቴክኒክ ስብሰባ

የቴክኒክ ስብሰባ ጥር 21 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡ዐዐ ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

አንቀጽ ሃያ

የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቡድን ኮታ

 1. የትግራይ ክልል 22 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 2. አማራ ክልል 22 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 3. ኦሮሚያ ክልል 22 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 4. ደቡብ ክልል 22 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 5. አዲስ አበባ አስተዳደር 22 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 6. ሐረሪ ክልል 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 7. ድሬዳዋ አስተዳደር 10 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 8. ጋምቤላ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 9. አፋር ክልል 8 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 1. ሱማሌ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ፤
 2. ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 15 ሰው ቡድን መሪና አሰልጣኝን ጨምሮ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከተሰጠው ኮታ በላይ ክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ በራሱ ወጪ ይሳተፋል፡፡

የፌዴሬሽኑ አድራሻዎች

ፋክስ፡ -    0116 45 08 79 የተወዳዳሪዎችን ዝርዝር በዚህ አድራሻ መላክ ይቻላል፡፡

E-mail This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ኢ-ሜል፡- eth@ ከውድድሩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በዚህ ኢ-ሜል አድራሻ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ድረ-ገፅ፡-   www.eaf.org.et የውድድር ደንቡን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል፡፡

 
   

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

33ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ኘሮግራም

 

ቀን፡ - ጥር 22/2ዐዐ8 ዓ.ም.

ቦታ፡ - ጃንሜዳ

ተ.ቁ ሰዓት ክንውን አፈፃፀም
1. 12፡30 የውድድሩ ስፍራ ለተመልካቾች ክፍት ይሆናል በኢት/አት/ፌዴሬሽን
2. 1፡30 የ6 ኪ.ሜ. ወጣት ሴቶች የስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
3. 2፡00 የ6 ኪ.ሜ. ወጣት ሴቶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
4. 2፡15 የ8 ኪ.ሜ. ወጣት ወንዶች የስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
5. 2፡40 የ8 ኪ.ሜ. ወጣት ወንዶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
6. 3፡10 የ8 ኪ.ሜ. የአዋቂ ሴቶች ስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
7. 3፡20 የ6 ኪ.ሜ. ወጣት ሴቶች ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
8. 3፡40 የ8 ኪ.ሜ. አዋቂ ሴቶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
9. 4፡00 የ12 ኪ.ሜ. አዋቂ ወንዶች ስም ጥሪ ይጀመራል በስም ጠሪ ዳኞች
10. 4፡20 የ8 ኪ.ሜ. ወጣት ወንዶች ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
11. 4፡35 የ12 ኪ.ሜ. አዋቂ ወንዶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
12. 5፡50 የ8 ኪ.ሜ. አዋቂ ሴቶች ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
13. 6፡00 የ12 ኪ.ሜ. አዋቂ ወንዶች ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
14. 6፡10 የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል በሽልማት ኮሚቴ
15. 6፡20 የውድድሩ ፍፃሜ ይሆናል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን


33ኛው ጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር

የተወዳዳሪ አትሌቶች መመዝገቢያ ቅጽ

ክልል፣ ከተማ አስተዳደር፣ ክለብና ማሠልጠኛ ማዕከል ________________________________________

 

ተ.ቁ. 6 ኪ.ሜ. ወጣት ሴቶች ተ.ቁ. 8 ኪ.ሜ. አዋቂ ሴቶች
1.   1.  
2.   2.  
3.   3.  
4.   4.  
5.   5.  
6.   6.  
7.   7.  
8.   8.  
9.   9.  
10.   10.  
11.   11.  
12.   12.  
ተ.ቁ. 8 ኪ.ሜ. ወጣት ወንዶች ተ.ቁ. 12 ኪ.ሜ. አዋቂ ወንዶች
1.   1.  
2.   2.  
3.   3.  
4.   4.  
5.   5.  
6.   6.  
7.   7.  
8.   8.  
9.   9.  
10.   10.  
11.   11.  
12.   12.  

ቅጹን የሞላው ስም ____________________________________________ ፊርማ _______________________

ቀን _________________________________

9ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር

ሕግና ደንብ

 

የውድድሩ ዓላማ

 1. እ.ኤ.አ. ማርች 26/2016 እንግሊዝ /ካርዲፋ/ ለሚደረገው የአለም ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ አትሌቶች ለመምረጥ፤
 2. ለክልሎች ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች የጐዳና ላይ ሩጫ ውድድር ዕድል ለመፍጠር፤
 3. ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤

አንቀጽ አንድ

አጠቃላይ የውድድር ደንብ

 1. የውድድሩ ስያሜ፡- ይህ ውድድር 9ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተብሎ ይጠራል፡፡
 2. ውድድሩ የሚመራው፡- ይህ ውድድር በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና በIAAF ሕግና ደንብ ይመራል፡፡

አንቀጽ ሁለት

የውድድሩ ርቀት

የውድድሩ ርቀት 21 ኪ.ሜ ነው፡፡

አንቀጽ ሦስት

የውድድሩ ቀንና ቦታ

9ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 06 ቀን 2ዐዐ8 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በሰበታ መንገድ ላይ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

አንቀጽ አራት

የዕድሜ ገደብ

ማንኛውም የግማሽ ማራቶን ተወዳዳሪ አትሌት ቢያንስ ዕድሜው ከ18 ዓመትና በላይ መሆን አለበት፡፡ ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ ተወዳዳሪ በውድድሩ መሳተፍ አይችልም፡፡

አንቀጽ አምስት

የምዝገባ ጊዜ

የምዝገባ ጊዜ ከጥር 23-30/2008 ዓ.ም. እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ጉርድ ሾላ በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ የምዝገባ ቀን ያሳለፈ ተሳታፊ ቡድን 300.00 ብር / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የካቲት 01/2006 ዓ.ም. ብቻ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ ይችላል፡፡

አንቀጽ ስድስት

የውድድሩ ተሳታፊዎች

 

በውድድሩ በሁለቱም ጾታ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ተቋማትና የግል ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

አንቀጽ ሰባት

በስም ጥሪ ቦታ መታወቂያ ወይም ፖስፓርት ይዞ መቅረብ

አትሌቶች በስም ጥሪ ቦታ በዘመኑ የታደሰ የክልላቸው/ከተማ አስተዳደራቸው ነዋሪ መሆናቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እንዲሁም የክለብ አትሌቶች የክለባቸውን ቴሴራ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

 

አንቀጽ ስምንት

የመወዳዳሪያ ቁጥር

የመወዳደሪያ ቁጥር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይሰጣል፡፡ ያለመወዳደሪያ ቁጥር መወዳደር አይቻልም፡፡ ተወዳድሮ ቢገኝ ውጤቱ ይሰረዛል፡፡ ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቁጥሩን በደረትና በጀርባው ላይ በሚታይ መልኩ መለጠፍ አለበት፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ

የውድድር አለባበስ

ማንኛውም ተወዳዳሪ የክልሉን፣ የከተማ አስተዳደሩን፤ የክለቡንና የተቋሙን ዩኒፎርም የሆነውን መለያ ለብሶ መወዳደር አለበት፡፡

አንቀጽ አስር

የአትሌቱ ጤንነት

በውድድሩ ተካፋይ የሚሆኑ አትሌቶች ጤንነታቸው የተሟላ መሆን አለባቸው፡፡ የጤንነት ችግር ያለባቸው አትሌቶች ተሰልፈው ቢገኙና ጉዳት ቢደርስባቸው ተጠያቂ የሚሆነው እራሱ ክልሉ/ ከተማ መስተዳድሩ /ክለቡ ወይም አትሌቱ ብቻ ይሆናሉ፡፡

 

 

 

አንቀጽ አስራ አንድ

የሥነ-ሥርዓት ጉድለት

ማንኛውም ተወዳዳሪ፣ አሰልጣኝ ፣ቡድን መሪ ፣አትሌት፣ ወጌሻ፣ ወይም የቡድኑ አባላት ወድድሩ በሚከናወንበት ወቅት የስነ-ስርዓት ጉድለት ካሳየና ውድድሩን በሚመሩ ዳኞችና የውድድር አመራሮች ሪፖርት ቀርቦ ጥፋቱ ከተረጋገጠ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በተዘጋጀው የአሠልጣኞች አትሌቶችና የክለቦች የሥነ-ምግባር ደንብ አንቀጽ አስር መሠረት ይቀጣል፡፡

አንቀጽ አስራ ሁለት

የቡድን ውጤት

ተወዳዳሪ ቡድኖች ካስመዘገቡት ስድስት አትሌቶች ውስጥ ቀድመው ለገቡ አራቱ አትሌቶች ነጥብ ይሰጣል፡፡ በቡድን አሰጣጥ ከአነስተኛ ወደ ከፍተኛ ቁጥር የገቡበት ደረጃ ተደምሮ አነስተኛ ድምር ያስመዘገበ ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡ የውጤት ድምራቸው እኩል ሲሆን መጨረሻ ነጥብ ያስመዘገበ /ዘጊው አትሌት/ ማለት በቡድኑ ቀድሞ ውድድሩን ላጠናቀቀ የቀረበው አትሌት ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡

ምሳሌ፡-

 • ቡድን “ሀ” 1ኛ፣ 5ኛ፣ 8ኛ፣ 9ኛ ቢወጡ ድምራቸው 23 ይሆናል፡፡
 • ሁለቱ “ለ” 2ኛ፣ 3ኛ፣ 6ኛ፣ 12ኛ ቢወጡ ድምራቸው 23 ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ቡድኖች ነጥባቸው እኩል ቢሆኑም ለአንደኛነት የቀረበው የመጨረሻ /ዘጊው አትሌት/ 9ኛ የወጣ የ “ሀ” ቡድን ስለሆነ የ “ሀ” ቡድን አሸናፊ ይሆናል፡፡
 • ከአራት በታች ውጤት ያስመዘገቡ ክልሎች፣ ከተማ መስተዳድሮችና ክለቦች የቡድን ድምር ውጤት ነጥብ ባይመዘገብላቸውም ባላቸው ውጤት አትሌቶች በግል ይሸለማሉ፡፡

አንቀጽ አስራ ሶስት

ክስና አቤቱታ ስለማቅረብ

 1. የአትሌት ተገቢነት የክስ ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው ውድድሩ ከመጀመሩ ከ3ዐ ደቂቃ በፊት ነው፡፡ የውድድር ውጤቶችን በተመለከተ የውድድሩ ውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ በ3ዐ ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ የውድድር ዳኛ ውሳኔውን መስጠት ወይም ጉዳዩን ከክስ ሰማ ኮሚቴ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በዳኛው ውሳኔ ያልተስማማ ቡድን በጽሁፍ ከብር ከ300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ጋር ለክስ ሰሚ ኮሚቴ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 2. ክሱ በክስ ሰሚ ኮሚቴ ተጣርቶ ተገቢ ክስ ሆኖ ከተገኘ የተያዘው ብር ተመላሽ ሆኖ ክሱ ተቀባይነት ይኖረዋል ፡፡ ነገር ግን ክሱ ተቀባይነት ካላገኘ የተያዘው ብር ለፌዴሬሽኑ ገቢ ሆኖ ውሳኔው የፀና ይሆናል ፡፡

        

አንቀጽ አስራ አራት

ሽልማት

 1. ለቡድን አሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማት በሁለቱም ጾታ፤
 2. በግል ከ1-6 ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት በሁለቱም ጾታ፤
 3. ከ1ኛ-3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፡፡

አንቀጽ አስራ አምስት

የቴክኒክ ስብሰባ

የቴክኒክ ስብሰባ የካቲት 05/2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድዮም ይካሄዳል፡፡ የተወዳዳሪ ለውጥ በቴክኒክ ስብሰባ ቀን ይከናወናል፡፡

አንቀጽ አስራ ስድስት

የክልሎችና የከተማ አስተዳድሮች ኮታ

 1. ለትግራይ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 2. ለአማራ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 3. ለኦሮሚያ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 4. ለደቡብ ክልል 8 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 5. ለሐረሪ ክልል 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 6. ድሬደዋ አስተዳደር 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 7. ለአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር 8 ሰው አበልና ትራንስፖርት ጨምሮ
 8. ለቤንሻንጉል ጉሙዝ 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 9. ለጋምቤላ 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 10. ለአፋር ክልል 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ፤
 11. ለሱማሌ ክልል 4 ሰው ቡድን መሪ እና አሰልጣኝ ጨምሮ ሲሆን፤ አበልና ትራንስፖርት ፌዴሬሽኑ ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን ከተሰጠው ኮታ ውጪ ክልሎች ወይም ከተማ አስተዳደሮች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ፡፡

9ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር ኘሮግራም

 

ቀን፡ - የካቲት 06/2ዐዐ8 ዓ.ም.

ቦታ፡ - በኦሮሚያ ክልል/ሰበታ/

ተ.ቁ ሰዓት ክንውን አፈፃፀም
1. 1፡00 የውድድሩ ስፍራ ለተመልካቾች ክፍት ይሆናል በውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ
2. 1፡15 የሴት ለተወዳዳሪዎች ስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
3. 1፡30 የወንድ ተወዳዳሪዎች ስም ጥሪ ይደረጋል በስም ጠሪ ዳኞች
4. 1፡45 የሴቶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
5. 2፡00 የወንዶች ውድድር ይጀመራል በአስነሺ ዳኞች
6. 4፡00 ለአሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል በተጋባዥ እንግዶች
7. 4፡20 ለአሸናፊዎች የዋንጫ ሽልማት ይሰጣል በዕለቱ የክብር እንግዳ
8. 4፡30 የውድድሩ ፍፃሜ ይሆናል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

 

 

 

 


Website by REMHAI ICT Solutions and Consulting